መሳፍንት 21:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)14 በዚያም ጊዜ የብንያም ልጆች ወደ እስራኤል ልጆች ተመለሱ፤ የእስራኤልም ልጆች ከኢያቢስ ገለዓድ ሴቶች ያዳኑአቸውን ሴቶች ሰጡአቸው። በዚህም ተስማሙ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም14 ስለዚህ በዚህ ጊዜ ብንያማውያን ተመለሱ፤ ከመገደል የተረፉትንም የኢያቢስ ገለዓድ ሴቶች ሰጧቸው፤ ይሁን እንጂ የሴቶቹ ቍጥር ለሁሉም የሚበቃ አልነበረም። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)14 ስለዚህ በዚህን ጊዜ ብንያማውያን ተመለሱ፤ ከመገደል የተረፉትንም የኢያቢስ ገለዓድ ሴቶች ሰጧቸው፤ ይሁን እንጂ የሴቶቹ ቊጥር ለሁሉም የሚበቃ አልነበረም። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም14 ብንያማውያንም ተመልሰው መጡ፤ ሌሎቹም እስራኤላውያን ከሞት በመትረፍ ከያቤሽ ተማርከው የመጡትን ልጃገረዶች ሰጡአቸው፤ ነገር ግን ቊጥራቸው ተመጣጣኝ ሆኖ አልተገኘም። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)14 በዚያም ጊዜ የብንያም ልጆች ተመለሱ፥ ከኢያቢስ ገለዓድም ሴቶች ያዳኑአቸውን ሴቶች አገቡአቸው። ነገር ግን የሚበቁ ሴቶች አላገኙም። 参见章节 |