Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 20:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

32 የብ​ን​ያ​ምም ልጆች፥ “እንደ ቀድ​ሞው በፊ​ታ​ችን ይሞ​ታሉ” አሉ። የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ግን፥ “እን​ሽሽ፤ ከከ​ተ​ማም ወደ መን​ገድ እና​ር​ቃ​ቸው” አሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

32 ብንያማውያኑ፣ “እንደ በፊቱ ይኸው ድል እያደረግናቸው ነው” አሉ፣ እስራኤላውያንም በበኩላቸው፣ “ወደ ኋላ እያፈገፈግን ከከተማዪቱ ወደ መንገዶቹ እንዲርቁ እናድርጋቸው” ይሉ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

32 ብንያማውያኑ፥ “እንደ በፊቱ ይሄው ድል እያደረግናቸው ነው” አሉ፥ እስራኤላውያንም በበኩላቸው፥ “ወደ ኋላ እያፈገፈግን ከከተማይቱ ወደ መንገዶቹ እንዲርቁ እናድርጋቸው” ይሉ ነበር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

32 ብንያማውያንም “ልክ ከዚህ በፊት እንዳደረግነው ፈጀናቸው” አሉ። እስራኤላውያን ግን “ወደ ኋላ አፈግፍገን ከከተማው ወደ አውራ ጐዳናው እናስወጣቸው” አሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

32 የብንያምም ልጆች፦ እንደ ቀድሞው በፊታችን ተመቱ አሉ። የእስራኤል ልጆች ግን፦ እንሽሽ፥ ከከተማም ወደ መንገድ እንሳባቸው አሉ።

参见章节 复制




መሳፍንት 20:32
6 交叉引用  

እኔ፥ ከእ​ኔም ጋር ያለው ሕዝብ ሁሉ ወደ ከተ​ማ​ዪቱ እን​ቀ​ር​ባ​ለን፤ የጋ​ይም ሰዎች እኛን ሊገ​ናኙ እንደ ፊተ​ኛው በወጡ ጊዜ ከፊ​ታ​ቸው እን​ሸ​ሻ​ለን፤


ወጥ​ተ​ውም በተ​ከ​ተ​ሉን ጊዜ ከከ​ተማ እና​ር​ቃ​ቸ​ዋ​ለን፤ እነ​ር​ሱም እንደ በፊቱ ከፊ​ታ​ችን ሸሹ ይላሉ፤ እኛም ከፊ​ታ​ቸው እን​ሸ​ሻ​ለን።


የብ​ን​ያ​ምም ልጆች በሕ​ዝቡ ላይ ወጡ፤ ከከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ሸሹ፤ እንደ ቀድ​ሞ​ውም ጊዜ፥ በአ​ው​ራ​ዎቹ መን​ገ​ዶች፥ አን​ደ​ኛው ወደ ቤቴል፥ ሁለ​ተ​ኛ​ውም ወደ ገባ​ዖን ሜዳ በሚ​ወ​ስ​ዱት መን​ገ​ዶች ላይ ሕዝ​ቡን ይመቱ፥ ይገ​ድ​ሉም ጀመር፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሠላሳ የሚ​ያ​ህሉ ሰዎች ነበሩ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች ሁሉ ከስ​ፍ​ራ​ቸው ተነ​ሥ​ተው በበ​ዓ​ል​ታ​ምር ተዋጉ። ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አድ​ፍ​ጠው የነ​በ​ሩት ከስ​ፍ​ራ​ቸው ከገ​ባ​ዖን ምዕ​ራብ ወጡ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አር​በ​ኞች ከሰ​ልፉ ተመ​ለሱ፤ ብን​ያ​ማ​ው​ያ​ንም እንደ ቀድ​ሞው ሰልፍ በፊ​ታ​ችን ተመ​ት​ተ​ዋል እያሉ ከእ​ስ​ራ​ኤል ሰዎች ሠላሳ የሚ​ያ​ህሉ ሰዎ​ችን መም​ታ​ትና መግ​ደል ጀመሩ።


跟着我们:

广告


广告