Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 20:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 በዚ​ያም ዘመን የአ​ሮን ልጅ የአ​ል​ዓ​ዛር ልጅ ፊን​ሐስ በፊቷ ይቆም ነበ​ርና። “ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ከብ​ን​ያም ልጆች ጋር ለመ​ዋ​ጋት ዳግ​መኛ እን​ው​ጣን? ወይስ እን​ቅር?” አሉ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ነገ በእ​ጃ​ችሁ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና ውጡ” አላ​ቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 የአሮን ልጅ፣ የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስም በፊቱ ይቆም ነበር። እስራኤላውያንም፣ “ወንድሞቻችንን ብንያማውያንን እንደ ገና ሄደን ጦርነት እንግጠማቸው ወይስ ይቅር?” ሲሉ ጠየቁ። እግዚአብሔርም፣ “ሂዱ፤ በነገው ዕለት በእጃችሁ እሳልፌ እሰጣችኋለሁ” አላቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 የአሮን ልጅ፤ የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስም በፊቱ ይቆም ነበር። እስራኤላውያንም፥ “ወንድሞቻችንን ብንያማውያንን እንደገና ሄደን ጦርነት እንግጠማቸው ወይስ ይቅር?” ሲሉ ጠየቁ። ጌታም፥ “ሂዱ፤ በነገው ዕለት በእጃችሁ እሳልፌ እሰጣችኋለሁ” አላቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 በዚያን ዘመን የአሮን ልጅ የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስ በእግዚአብሔር ፊት ያገለግል ስለ ነበረ እግዚአብሔርን ጠየቀ፦ “ወንድሞቻችንን ብንያማውያንን ለመውጋት እንደገና እንውጣን ወይስ እንቅር” ብሎ ጠየቀ። እግዚአብሔርም፥ “ነገ በእነርሱ ላይ ድልን እንድትቀዳጁ አደርጋለሁና ሂዱና ውጉአቸው!” አለ።

参见章节 复制




መሳፍንት 20:28
21 交叉引用  

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ታቦት በአ​ዲስ ሰረ​ገላ ላይ ጫኑ​አት፥ በኮ​ረ​ብ​ታ​ውም ላይ ከነ​በ​ረው ከአ​ሚ​ና​ዳብ ቤት አመ​ጡ​አት፤ የአ​ሚ​ና​ዳብ ልጆ​ችም ዖዛና ወን​ድ​ሞቹ ታቦቷ ያለ​ች​በ​ትን ሰረ​ገላ ይነዱ ነበር።


እና​ንተ የም​ቷጉ አይ​ደ​ላ​ች​ሁም፤ ይሁ​ዳና ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሆይ፥ ተሰ​ለፉ፤ ዝም ብላ​ችሁ ቁሙ፤ የሚ​ሆ​ነ​ው​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ማዳን እዩ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ና​ንተ ጋር ነውና አት​ፍሩ፤ አት​ደ​ን​ግ​ጡም፤ ነገም ውጡ​ባ​ቸው።”


የአ​ቢሱ ልጅ፥ የፊ​ን​ሐስ ልጅ፥ የአ​ል​ዓ​ዛር ልጅ፥ የመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ካህን የአ​ሮን ልጅ፥


የአ​ሮ​ንም ልጅ አል​ዓ​ዛር ከፋ​ት​ኤል ልጆች ሚስ​ትን አገባ፤ እር​ስ​ዋም ፊን​ሐ​ስን ወለ​ደ​ች​ለት። እነ​ዚ​ህም በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው የሌ​ዋ​ው​ያን አባ​ቶች አለ​ቆች ናቸው።


አቤቱ! የሰው መን​ገድ ከራሱ እንደ አይ​ደለ አው​ቃ​ለሁ፤ ሰውም አይ​ሄ​ድ​ባ​ትም፤ መን​ገ​ዱ​ንም ጥር​ጊያ አላ​ደ​ረ​ገም።


በዚ​ያን ጊዜ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ኪዳን ታቦት ይሸ​ከም ዘንድ፥ እር​ሱ​ንም ለማ​ገ​ል​ገል በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ይቆም ዘንድ፥ በስ​ሙም ይባ​ርክ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እስከ ዛሬ ድረስ የሌ​ዊን ነገድ ለየ።


እርሱ ከል​ጆቹ ጋር በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቁሞ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ያገ​ለ​ግል ዘንድ፥ በስ​ሙም ይባ​ርክ ዘንድ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከነ​ገ​ዶ​ችህ ሁሉ መር​ጦ​ታ​ልና።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በገ​ለ​ዓድ ምድር ወዳ​ሉት ወደ ሮቤል ልጆ​ችና ወደ ጋድ ልጆች ወደ ምና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ የካ​ህኑ የአ​ሮ​ንን ልጅ የአ​ል​ዓ​ዛ​ርን ልጅ ፊን​ሐ​ስን ላኩ።


የአ​ሮ​ንም ልጅ ሊቀ ካህ​ናቱ አል​ዓ​ዛር ሞተ፤ በተ​ራ​ራ​ማ​ውም በኤ​ፍ​ሬም ሀገር ለልጁ ለፊ​ን​ሐስ በተ​ሰ​ጠ​ችው በጊ​ብ​ዓት መሬት ቀበ​ሩት።


ኢያ​ሱም አለ፥ “ወዮ! ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ! በአ​ሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያን እጅ አሳ​ል​ፈህ ትሰ​ጠን፥ ታጠ​ፋ​ንም ዘንድ አገ​ል​ጋ​ይህ ይህን ሕዝብ ዮር​ዳ​ኖ​ስን ለምን አሻ​ገረ? በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ ተቀ​ም​ጠን በኖ​ርን ነበር እኮ!


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ይሁዳ ይውጣ፤ እነሆ፥ ምድ​ሪ​ቱን በእጁ አሳ​ልፌ ሰጥ​ቼ​አ​ታ​ለሁ” አለ።


እነ​ሆም አንድ ሽማ​ግሌ ከእ​ር​ሻው ሥራ ወደ ማታ መጣ፤ ይህም ሰው ከተ​ራ​ራ​ማው ከኤ​ፍ​ሬም ሀገር ነበረ፤ በገ​ባ​ዖ​ንም በእ​ን​ግ​ድ​ነት ተቀ​ምጦ ነበር፤ የዚያ ሀገር ሰዎች ግን የብ​ን​ያም ልጆች ነበሩ።


በዚ​ያ​ችም ሌሊት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ “በእ​ጅህ አሳ​ልፌ ሰጥ​ቻ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና ተነ​ሥ​ተህ ወደ ሰፈር ውረድ።


ሳኦ​ልም፥ “ልው​ረ​ድና ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን ልከ​ተ​ልን? በእ​ስ​ራ​ኤ​ልስ እጅ አሳ​ል​ፈህ ትሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለ​ህን?” ብሎ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጠየ​ቀው። በዚያ ቀን ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አል​መ​ለ​ሰ​ለ​ትም።


ዳዊ​ትም፥ “የእ​ነ​ዚ​ህን ሠራ​ዊት ፍለጋ ልከ​ተ​ልን? አገ​ኛ​ቸ​ዋ​ለ​ሁን?” ብሎ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጠየቀ፤ እር​ሱም፥ “ታገ​ኛ​ቸ​ዋ​ለ​ህና፥ ፈጽ​መ​ህም ምር​ኮ​ኞ​ቹን ታድ​ና​ለ​ህና ፍለ​ጋ​ቸ​ውን ተከ​ተል” ብሎ መለ​ሰ​ለት።


跟着我们:

广告


广告