መሳፍንት 20:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)25 በሁለተኛውም ቀን የብንያም ልጆች ሊገጥሙአቸው ከገባዖን ወጡ፤ ከእስራኤልም ልጆች ደግሞ ዐሥራ ስምንት ሺህ ሰዎችን በምድር ላይ ገደሉ፤ እነዚህም ሁሉ ሰይፍ የሚመዝዙ ነበሩ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም25 በዚሁ ጊዜም ብንያማውያን፣ እስራኤላውያንን ሊወጉ ከጊብዓ ወጡ፤ እንደ ገናም በሙሉ ሰይፍ የታጠቁ ዐሥራ ስምንት ሺሕ ሰዎች ገደሉ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)25 በዚሁ ጊዜም ብንያማውያን፥ እስራኤላውያንን ሊወጉ ከጊብዓ ወጡ፤ እንደገናም በሙሉ ሰይፍ የታጠቁ ዐሥራ ስምንት ሺህ ሰዎች ገደሉ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም25 እንዲሁም ብንያማውያን በሁለተኛው ቀን ከጊብዓ ወጡ፤ በዚህም ጊዜ ዐሥራ ስምንት ሺህ የሠለጠኑ የእስራኤላውያንን ወታደሮች ገደሉ፤ 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)25 በሁለተኛውም ቀን ብንያም ከጊብዓ በእነርሱ ላይ ወጣ፥ ከእስራኤልም ልጆች ደግሞ አሥራ ስምንት ሺህ ሰዎች ገደሉ፥ እነዚህም ሁሉ ሰይፍ የሚመዝዙ ነበሩ። 参见章节 |