Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 20:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች ተበ​ራቱ፤ በፊ​ተ​ኛ​ውም ቀን በተ​ሰ​ለ​ፉ​በት ስፍራ ደግ​መው ተሰ​ለፉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ይሁን እንጂ እስራኤላውያን እርስ በርሳቸው ተበረታትተው በመጀመሪያው ቀን ተሰልፈው በነበረበት ስፍራ ላይ እንደ ገና ቦታ ቦታቸውን ያዙ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ይሁን እንጂ እስራኤላውያን እርስ በርሳቸው ተበረታትተው በመጀመሪያው ቀን ተሰልፈው በነበረበት ስፍራ ላይ እንደገና ቦታ ቦታቸውን ያዙ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 የእስራኤልም ሠራዊት ተበራቱ፤ በመጀመሪያው ቀን በተሰለፉበትም ስፍራ ደግመው ተሰለፉ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ሕዝቡም፥ የእስራኤል ሰዎች፥ ተበራቱ፥ በፊተኛውም ቀን በተሰለፉበት ስፍራ ደግመው ተሰለፉ።

参见章节 复制




መሳፍንት 20:22
7 交叉引用  

ዳዊ​ትም መል​እ​ክ​ተ​ኛ​ውን፥ “ሰይፍ አንድ ጊዜ ይህን፥ አንድ ጊዜም ያን ይበ​ላ​ልና ይህ ነገር በዐ​ይ​ንህ አይ​ክፋ፤ ከተ​ማ​ዪ​ቱን የሚ​ወ​ጉ​ትን አበ​ርታ፤ አፍ​ር​ሳ​ትም ብለህ ለኢ​ዮ​አብ ንገ​ረው፤ አን​ተም አጽ​ናው” አለው።


ቤተ መቅ​ደ​ስህ ቅዱስ ነው በጽ​ድ​ቅም ድንቅ ነው። በም​ድር ዳርቻ ሁሉና በሩቅ ባሕር ውስጥ ላሉ ተስ​ፋ​ቸው የሆ​ንህ፥ አም​ላ​ካ​ች​ንና መድ​ኃ​ኒ​ታ​ችን ሆይ ስማን።


በዚ​ያም ቀን ከየ​ከ​ተ​ማው የመጡ የብ​ን​ያም ልጆች ተቈ​ጠሩ፤ ቍጥ​ራ​ቸ​ውም ከገ​ባ​ዖን ሰዎች ሌላ ሃያ አም​ስት ሺህ ሰይፍ የሚ​መ​ዝዙ ሰዎች ነበሩ፤ ከገ​ባ​ዖ​ንም ሰባት መቶ የተ​መ​ረጡ ሰዎች ተቈ​ጠሩ፤


ከብ​ን​ያ​ምም ልጆች ሌላ የእ​ስ​ራ​ኤል ሰዎች አራት መቶ ሺህ ሰይፍ የሚ​መ​ዝዙ ሰዎች ተቈ​ጠሩ፤ እነ​ዚ​ህም ሁሉ ሰል​ፈ​ኞች ነበሩ።


የብ​ን​ያ​ምም ልጆች ከገ​ባ​ዖን ወጡ፤ በዚ​ያም ቀን ከእ​ስ​ራ​ኤ​ላ​ው​ያን ሃያ ሁለት ሺህ ሰዎ​ችን በም​ድር ላይ ገደሉ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ወጥ​ተው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እስከ ማታ ድረስ አለ​ቀሱ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም፥ “ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ከብ​ን​ያም ልጆች ጋር ለመ​ዋ​ጋት ዳግ​መኛ እን​ቀ​ር​ባ​ለን?” ብለው ጠየቁ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም “በእ​ነ​ርሱ ላይ ውጡ” አለ።


ስለ ወን​ዶ​ችና ስለ ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ውም የሕ​ዝቡ ሁሉ ልብ አዝኖ ነበ​ርና ሕዝቡ ሊወ​ግ​ሩት ስለ ተና​ገሩ ዳዊት እጅግ ተጨ​ነቀ፤ ዳዊት ግን በአ​ም​ላኩ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ራሱን አጽ​ናና።


跟着我们:

广告


广告