Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 20:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ተነ​ሥ​ተው ወደ ቤቴል ወጡ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም፥ “የብ​ን​ያ​ምን ልጆች ለመ​ው​ጋት መሪ ሆኖ ማን ይው​ጣ​ልን?” ብለው ጠየ​ቁት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ይሁዳ መሪ ይሁን” አለ፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 እስራኤላውያን ወደ ቤቴል ወጡ፤ እግዚአብሔርም፣ “ብንያማውያንን ለመውጋት ከመካከላችን ማን ቀድሞ ይውጣ?” ሲሉ ጠየቁ። እግዚአብሔርም፣ “ይሁዳ ቀድሞ ይውጣ” ብሎ መለሰ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 እስራኤላውያን ወደ ቤቴል ወጡ፤ እግዚአብሔርንም “ብንያማውያንን ለመውጋት ከመካከላችን ማን ቀድሞ ይውጣ?” ሲሉ ጠየቁ። ጌታም፥ “ይሁዳ ቀድሞ ይውጣ” ብሎ መለሰ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 እስራኤላውያን ወደ ቤትኤል ወጥተው “በብንያማውያን ላይ መጀመሪያ አደጋ መጣል የሚገባው የትኛው ነገድ ነው?” ሲሉ እግዚአብሔርን ጠየቁ። እግዚአብሔርም “የይሁዳ ነገድ አስቀድሞ ይዝመት” አላቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 የእስራኤልም ልጆች ተነሥተው ወደ ቤቴል ወጡ፥ እግዚአብሔርንም፦ የብንያምን ልጆች ለመውጋት አስቀድሞ ማን ይውጣልን? ብለው ጠየቁት፥ እግዚአብሔርም፦ ይሁዳ ይቅደም አለ።

参见章节 复制




መሳፍንት 20:18
15 交叉引用  

ጾምን ቀድሱ፤ ምህ​ላ​ንም ዐውጁ፤ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ቹ​ንና በም​ድር የሚ​ኖ​ሩ​ትን ሁሉ ወደ አም​ላ​ካ​ችን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ሰብ​ስቡ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በአ​ን​ድ​ነት ጩኹ።


በካ​ህ​ኑም በአ​ል​ዓ​ዛር ፊት ይቁም፤ እር​ሱም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ፍርድ ይጠ​ይ​ቅ​ለት፤ እርሱ ከእ​ር​ሱም ጋር የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ማኅ​በር ሁሉ በቃሉ ይውጡ፤ በቃ​ሉም ይግቡ።”


በአ​ባ​ታ​ችን ወን​ድ​ሞች መካ​ከል ርስ​ትን ስጠን።” ሙሴም ነገ​ራ​ቸ​ውን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አቀ​ረበ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ማኅ​በር ሁሉ በሴሎ ተሰ​በ​ሰቡ፤ በዚ​ያም የም​ስ​ክ​ሩን ድን​ኳን ተከሉ፤ ምድ​ሩም ጸጥ ብሎ ተገ​ዛ​ላ​ቸው።


አለ​ቆ​ችም ከስ​ን​ቃ​ቸው ወሰዱ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አል​ጠ​የ​ቁም።


ሚካም ያደ​ረ​ገ​ውን የተ​ቀ​ረፀ ምስል የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በሴሎ ባለ​በት ዘመን ሁሉ አቆሙ።


እር​ሱም፥ “እኛ ከይ​ሁዳ ቤተ ልሔም ወደ ተራ​ራ​ማው ወደ ኤፍ​ሬም ሀገር ማዶ እና​ል​ፋ​ለን፤ እኔ ከዚያ ነኝ፤ ወደ ይሁዳ ቤተ ልሔ​ምም ሄጄ ነበር፥ አሁ​ንም ወደ ቤቴ እሄ​ዳ​ለሁ፤ በቤ​ቱም የሚ​ያ​ሳ​ድ​ረኝ አጣሁ፤


ከብ​ን​ያ​ምም ልጆች ሌላ የእ​ስ​ራ​ኤል ሰዎች አራት መቶ ሺህ ሰይፍ የሚ​መ​ዝዙ ሰዎች ተቈ​ጠሩ፤ እነ​ዚ​ህም ሁሉ ሰል​ፈ​ኞች ነበሩ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በማ​ለዳ ተነ​ሥ​ተው በገ​ባ​ዖን ፊት ሰፈሩ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ወጥ​ተው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እስከ ማታ ድረስ አለ​ቀሱ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም፥ “ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ከብ​ን​ያም ልጆች ጋር ለመ​ዋ​ጋት ዳግ​መኛ እን​ቀ​ር​ባ​ለን?” ብለው ጠየቁ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም “በእ​ነ​ርሱ ላይ ውጡ” አለ።


እነሆ፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሆይ፥ ሁላ​ችሁ፥ ምክ​ራ​ች​ሁ​ንና እዝ​ና​ታ​ች​ሁን በዚህ ስጡ።”


ከዚ​ያም ደግሞ አል​ፈህ፥ ወደ ትልቁ የታ​ቦር ዛፍ ትደ​ር​ሳ​ለህ፤ በዚ​ያም ሦስት ሰዎች፥ አንዱ ሦስት የፍ​የል ጠቦ​ቶች ሲነዳ፥ ሁለ​ተ​ኛው ሦስት የዳቦ ስልቻ፥ ሦስ​ተ​ኛ​ውም የወ​ይን ጠጅ አቁ​ማዳ ይዘው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ ቤቴል ሲወጡ ታገ​ኛ​ለህ፤


跟着我们:

广告


广告