Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 2:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ተቈጣ፤ ወደ ማረ​ኳ​ቸ​ውም ማራ​ኪ​ዎች እጅ አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው፤ ማረ​ኩ​አ​ቸ​ውም፤ በዙ​ሪ​ያ​ቸ​ውም ባሉት በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸው እጅ አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው፤ ከዚ​ያም ወዲያ ጠላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ሊቋ​ቋሙ አል​ቻ​ሉም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 እግዚአብሔር በእስራኤል ላይ በመቈጣቱ ለሚዘርፏቸው አሳልፎ ሰጣቸው፤ በዙሪያቸው ላሉ ጠላቶቻቸው ሸጣቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ስለዚህ ጌታ በእስራኤል ላይ በመቈጣቱ ለሚዘርፏቸው አሳልፎ ሰጣቸው፤ በዙሪያቸው ላሉ ጠላቶቻቸው ሸጣቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ከዚህም የተነሣ እግዚአብሔር በእስራኤል ላይ በጣም ተቈጣ፤ እንዲዘርፉአቸውም ለወራሪዎች አሳልፎ ሰጣቸው፤ በዙሪያቸው ያሉ ጠላቶቻቸውም እንዲበረቱባቸው አደረገ። ከዚያም በኋላ እስራኤላውያን ከጠላቶቻቸው ወረራ ራሳቸውን መከላከል ተሳናቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 የእግዚአብሔርም ቁጣ በእስራኤል ላይ ነደደ፥ ወደ ማረኩአቸውም ማራኪዎች እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፥ በዙሪያቸውም ባሉት በጠላቶቻቸው እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፥ ጠላቶቻቸውንም ከዚያ ወዲያ ሊቋቋሙ አልቻሉም።

参见章节 复制




መሳፍንት 2:14
35 交叉引用  

ደግ​ሞም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ነደደ፤ ዳዊ​ት​ንም፥ “ሂድ፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንና ይሁ​ዳን ቍጠር” ብሎ በላ​ያ​ቸው አስ​ነ​ሣው።


በሕ​ዝቤ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ፈራ​ጆ​ችን በሾ​ምሁ ጊዜ ከጠ​ላ​ቶ​ችህ ሁሉ አሳ​ር​ፍ​ሃ​ለሁ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ደግሞ፦ ቤት እን​ደ​ም​ት​ሠ​ራ​ለት ይነ​ግ​ር​ሃል፤ እሠ​ራ​ለ​ታ​ለሁ ብለ​ሃ​ልና።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ በጣም ተቈጣ፤ በዘ​መ​ኑም ሁሉ በሶ​ር​ያው ንጉሥ በአ​ዛ​ሄል እጅ፥ በአ​ዛ​ሄ​ልም ልጅ በወ​ልደ አዴር እጅ አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ስ​ራ​ኤል ዘር ሁሉ ተቈጣ፤ አስ​ጨ​ነ​ቃ​ቸ​ውም፤ ከፊ​ቱም እስ​ኪ​ጥ​ላ​ቸው ድረስ በበ​ዝ​ባ​ዦች እጅ አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው።


በዚ​ያም ዘመን ለሚ​ወ​ጣ​ውና ለሚ​ገ​ባው ሰላም አይ​ሆ​ን​ለ​ትም፤ በሀ​ገ​ሮ​ችም በሚ​ኖ​ሩት ሁሉ ላይ ታላቅ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ ይሆ​ናል።


ስለ​ዚህ አም​ላኩ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሶ​ርያ ንጉሥ እጅ አሳ​ልፎ ሰጠው፤ እር​ሱም መታው፤ ከእ​ር​ሱም ብዙ ምር​ኮ​ኞ​ችን ወሰደ፤ ወደ ደማ​ስ​ቆም አመ​ጣው። ደግ​ሞም በእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ እጅ አሳ​ልፎ ሰጠው፤ እር​ሱም በታ​ላቅ አመ​ታት መታው።


እነ​ርሱ ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ በሕ​ዝቡ ላይ እስ​ኪ​ወጣ ድረስ፥ ፈው​ስም እስ​ከ​ማ​ይ​ገ​ኝ​ላ​ቸው ድረስ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​እ​ክ​ተ​ኞች ይሳ​ለቁ፥ ቃሉ​ንም ያቃ​ልሉ፥ በነ​ቢ​ያ​ቱም ላይ ያፌዙ ነበር።


ስለ​ዚህ በሚ​ያ​ሠ​ቃ​ዩ​አ​ቸው ሰዎች እጅ አሳ​ል​ፈህ ሰጠ​ሃ​ቸው፤ አስ​ጨ​ነ​ቋ​ቸ​ውም፤ በመ​ከ​ራ​ቸ​ውም ጊዜ ወደ አንተ ጮኹ፤ ከሰ​ማ​ይም ሰማ​ሃ​ቸው፤ እንደ ምሕ​ረ​ት​ህም ብዛት ታዳ​ጊ​ዎ​ችን ሰጠ​ሃ​ቸው፤ ከሚ​ያ​ሠ​ቃ​ዩ​አ​ቸ​ውም እጅ አዳ​ን​ሃ​ቸው።


ንጉሥ ውበ​ት​ሽን ወድ​ዶ​አ​ልና፥ እርሱ ጌታሽ ነውና።


የጢ​ሮስ ሴቶች ልጆች እጅ መን​ሻን ይዘው ይሰ​ግ​ዱ​ለ​ታል። የም​ድር ባለ​ጠ​ጎች አሕ​ዛብ ሁሉ በፊ​ትሽ ይማ​ለ​ላሉ።


ያዕ​ቆ​ብን እን​ዲ​ማ​ር​ኩት፥ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም እን​ዲ​በ​ዘ​ብ​ዙት ያደ​ረገ ማን ነው? እነ​ር​ሱም የበ​ደ​ሉት፥ በመ​ን​ገ​ዱም ይሄዱ ዘንድ ያል​ወ​ደ​ዱት፥ ሕጉ​ንም ያል​ሰ​ሙት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እርሱ አይ​ደ​ለ​ምን?


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “እና​ታ​ች​ሁን የፈ​ታ​ሁ​በት የፍ​ችዋ ደብ​ዳቤ የት አለ? ወይስ እና​ን​ተን የሸ​ጥሁ ከአ​በ​ዳ​ሪ​ዎች ለማን ነው? እነሆ፥ ስለ ኀጢ​አ​ታ​ችሁ ተሸ​ጣ​ች​ኋል፤ ስለ በደ​ላ​ች​ሁም እና​ታ​ችሁ ተፈ​ት​ታ​ለች።


ነገር ግን እና​ን​ተን የሚ​ወ​ጉ​ትን የከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ንን ጭፍራ ሁሉ ብት​መቱ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጥቂት ተወ​ግ​ተው ያል​ሞቱ ቢቀሩ ሁሉ እያ​ን​ዳ​ንዱ በስ​ፍ​ራው ይነ​ሣሉ፤ ይህ​ቺ​ንም ሀገር በእ​ሳት ያቃ​ጥ​ላሉ።”


ፊቴ​ንም አከ​ብ​ድ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ፊት ትወ​ድ​ቃ​ላ​ችሁ፤ የሚ​ጠ​ሏ​ች​ሁም ያሸ​ን​ፉ​አ​ች​ኋል። ማንም ሳያ​ሳ​ድ​ዳ​ችሁ ትሸ​ሻ​ላ​ችሁ።


እኔ ደግሞ አግ​ድሜ በቍጣ እሄ​ድ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ እንደ ኀጢ​አ​ታ​ች​ሁም ሰባት እጥፍ እቀ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ።


ማንም ሳያ​ሳ​ድ​ዳ​ቸው ከሰ​ይፍ እን​ዲ​ሸሹ እርስ በር​ሳ​ቸው ይሰ​ነ​ካ​ከ​ላሉ፤ እና​ን​ተም በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ችሁ ፊት መቆም አት​ች​ሉም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ በጠና ተቈጣ። በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ክፉ ያደ​ረገ ትው​ልድ ሁሉ እስ​ኪ​ጠፋ ድረስ አርባ ዓመት በም​ድረ በዳ ውስጥ አን​ከ​ራ​ተ​ታ​ቸው።


እነ​ሆም፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መዓት በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ አብ​ዝ​ታ​ችሁ ትጨ​ምሩ ዘንድ እና​ንተ በኀ​ጢ​አ​ተ​ኞች ሰዎች በደል በአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ ፋንታ ተነ​ሥ​ታ​ች​ኋል።


እኔን ስለ​ተ​ው​ኸኝ፥ ስለ ሥራህ ክፋት፥ እስ​ክ​ት​ጠፋ፥ ፈጥ​ነ​ህም እስ​ክ​ታ​ልቅ ድረስ በም​ት​ሠ​ራው ሥራ ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ችግ​ርን፥ ረኃ​ብን፦ ቸነ​ፈ​ር​ንም ይል​ክ​ብ​ሃል።


“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከጠ​ላ​ቶ​ችህ ፊት የተ​መ​ታህ ያደ​ር​ግ​ሃል፤ በአ​ንድ መን​ገድ ትወ​ጣ​ባ​ቸ​ዋ​ለህ፤ በሰ​ባት መን​ገ​ድም ከእ​ነ​ርሱ ትሸ​ሻ​ለህ፤ በም​ድ​ርም መን​ግ​ሥ​ታት ሁሉ የተ​በ​ተ​ንህ ትሆ​ና​ለህ።


“በዚህ መጽ​ሐፍ የተ​ጻ​ፉ​ትን የዚ​ህን ሕግ ቃሎች ሁሉ ታደ​ርግ ዘንድ፥ ይህ​ንም ክቡ​ርና ምስ​ጉን ስም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክ​ህን ትፈራ ዘንድ ባት​ሰማ፥


አንዱ ሽሁን እን​ዴት ያሳ​ድ​ዳ​ቸ​ዋል? ሁለ​ቱስ ዐሥ​ሩን ሽህ እን​ዴት ያባ​ር​ሩ​አ​ቸ​ዋል? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍዳ​ውን አም​ጥ​ቶ​ባ​ቸ​ዋ​ልና። አም​ላ​ካ​ች​ንም አሳ​ልፎ ሰጥ​ቶ​አ​ቸ​ዋ​ልና።


አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዘ​ዛ​ች​ሁን ቃል ኪዳን ብታ​ፈ​ርሱ፥ ሄዳ​ች​ሁም ሌሎ​ችን አማ​ል​ክት ብታ​መ​ልኩ፥ ብት​ሰ​ግ​ዱ​ላ​ቸ​ውም፥ በዚያ ጊዜ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ ይነ​ድ​ድ​ባ​ች​ኋል፥ ከሰ​ጣ​ች​ሁም ከመ​ል​ካ​ሚቱ ምድር ፈጥ​ና​ችሁ ትጠ​ፋ​ላ​ችሁ።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከይ​ሁዳ ጋር ነበረ፤ ይሁ​ዳም ተራ​ራ​ማ​ውን ሀገር ወረሰ፤ በሸ​ለ​ቆው የሚ​ኖ​ሩ​ትን ግን የብ​ረት ሰረ​ገ​ሎች ነበ​ሩ​አ​ቸ​ውና ሊወ​ር​ሳ​ቸው አል​ቻ​ለም።


አሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም የዳ​ንን ልጆች በተ​ራ​ራ​ማው ሀገር አስ​ጨ​ነ​ቁ​አ​ቸው፤ ወደ ሸለ​ቆው እን​ዲ​ወ​ርዱ አይ​ፈ​ቅ​ዱ​ላ​ቸ​ውም ነበ​ርና።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ፈጽሞ ተቈጣ፤ በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን እጅና በአ​ሞን ልጆች እጅም አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ፈጽሞ ተቈጣ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “ይህ ሕዝብ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ያዘ​ዝ​ሁ​ትን ቃል ኪዳን ስለ ተላ​ለፉ፥ ቃሌ​ንም ስላ​ል​ሰሙ፥


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እንደ ገና ክፉ ሥራ ሠሩ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ክፉ ስለ ሠሩ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሞ​ዓ​ብን ንጉሥ ዔግ​ሎ​ምን በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ አበ​ረ​ታ​ባ​ቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በአ​ሦር በነ​ገ​ሠው በከ​ነ​ዓን ንጉሥ በኢ​ያ​ቢን እጅ አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው፤ የሠ​ራ​ዊ​ቱም አለቃ ሲሣራ ነበረ፤ እር​ሱም በአ​ሕ​ዛብ አሪ​ሶት ይቀ​መጥ ነበረ።


跟着我们:

广告


广告