መሳፍንት 19:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)30 ከዚያም በኋላ ያያት ሁሉ እንዲህ አለ፥ “እስራኤል ከግብፅ ከወጡ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እንዲህ ያለ ነገር የሆነበት ጊዜ የለም፤ የታየበትም ጊዜ የለም፤” ያም ሰው እነዚያን የላካቸውን ሰዎች እንዲህ ብሎ አዘዛቸው፥ “የእስራኤልን ሰዎች እንዲህ በሏቸው፦ እስራኤል ከግብፅ ከወጡ ጊዜ ጀምሮ እስከ ዛሬ እንዲህ የሆነበት ጊዜ አለን? እናንተ ተመካከሩበት፤ የሚበጀውንም ተነጋገሩ።” 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም30 ያየም ሁሉ፣ “እስራኤላውያን ከግብጽ ከወጡ ጀምሮ እንዲህ ያለ ነገር ከቶ አልታየም፤ አልተደረገም፤ ምን ማድረግ እንዳለብንም በነገሩ አስቡበት፤ ተመካከሩበት” ተባባሉ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)30 ያየም ሁሉ፥ “እስራኤላውያን ከግብጽ ከወጡ ጀምሮ እንዲህ ያለ ነገር ከቶ አልታየም፤ አልተደረገም፤ ምን ማድረግ እንዳለብንም በነገሩ አስቡበት፤ ተመካከሩ በት” ተባባሉ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም30 ከዚያ በኋላ የላካቸውን ሰዎች እንዲህ ብሎ አዘዛቸው፦ “ለእስራኤላውያን ሁሉ እንዲህ በሉአቸው፦ ‘የእስራኤል ሕዝብ ከግብጽ ምድር ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እንዲህ ያለ ነገር ተደርጎ ያውቃልን? አስቡበት፤ ተመካከሩበት ተነጋገሩበትም።’ ” ያዩት ሁሉ “እስከዚህ ጊዜ ድረስ እንዲህ ያለ ነገር ታይቶም አይታወቅ!” አሉ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)30 ያየም ሁሉ፦ የእስራኤል ልጆች ከግብፅ ምድር ከወጡ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እንዲህ ያለ ነገር ከቶ አልተደረገም፥ አልታየምም፥ አስቡት፥ በዚህም ተመካከሩ፥ ተነጋገሩም ይባባል ነበር። 参见章节 |