Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 19:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 በገ​ባ​ዖ​ንም ገብ​ተው ያድሩ ዘንድ ወደ​ዚያ አቀኑ። ገብ​ተ​ውም በከ​ተ​ማው አደ​ባ​ባይ በተ​ቀ​መጡ ጊዜ ወደ ቤቱ የሚ​ያ​ስ​ገ​ባ​ቸ​ውና የሚ​ያ​ሳ​ድ​ራ​ቸው አል​ነ​በ​ረም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ለማደርም ወደዚያው ጐራ አሉ፤ ሄደውም በከተማዪቱ አደባባይ ተቀመጡ፤ ሆኖም በቤቱ ለማሳደር ማንም አልተቀበላቸውም ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ለማደርም ወደዚያው ጎራ አሉ፤ ሄደውም በከተማይቱ አደባባይ ተቀመጡ፤ ሆኖም በቤቱ ለማሳደር ማንም አልተቀበላቸውም ነበር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 የሚያድሩበትንም ስፍራ ፈልገው ለማግኘት ከመንገድ ወጣ አሉ፤ ወደ ከተማይቱም ገብተው በአደባባዩ አጠገብ ተቀመጡ፤ ነገር ግን ወደ ቤት ወስዶ የሚያሳድራቸው ማንንም አላገኙም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 በጊብዓም ገብተው ያድሩ ዘንድ ወደዚያ አቀኑ። በገባም ጊዜ ሊያሳድራቸው ማንም በቤቱ አልተቀበላቸውምና በከተማው አደባባይ ተቀመጡ።

参见章节 复制




መሳፍንት 19:15
9 交叉引用  

ተርቤ አብልታችሁኛልና፤ ተጠምቼ አጠጥታችሁኛልና፤ እንግዳ ሆኜ ተቀብላችሁኛልና፤ ታርዤ አልብሳችሁኛልና፤


እንግዳ ሆኜ አልተቀበላችሁኝምና፤ ታርዤ አላለበሳችሁኝምና፤ ታምሜ ታስሬም አልጠየቃችሁኝምና።’


እን​ግዳ መቀ​በ​ል​ንም አት​ርሱ፤ በዚህ ምክ​ን​ያት ሳያ​ውቁ መላ​እ​ክ​ትን በእ​ን​ግ​ድ​ነት ለመ​ቀ​በል ያታ​ደሉ አሉና።


አል​ፈ​ውም ሄዱ፤ የብ​ን​ያ​ምም ነገድ በም​ት​ሆ​ነው በገ​ባ​ዖን አጠ​ገብ ሳሉ ፀሐይ ገባ​ች​ባ​ቸው።


እነ​ሆም አንድ ሽማ​ግሌ ከእ​ር​ሻው ሥራ ወደ ማታ መጣ፤ ይህም ሰው ከተ​ራ​ራ​ማው ከኤ​ፍ​ሬም ሀገር ነበረ፤ በገ​ባ​ዖ​ንም በእ​ን​ግ​ድ​ነት ተቀ​ምጦ ነበር፤ የዚያ ሀገር ሰዎች ግን የብ​ን​ያም ልጆች ነበሩ።


እር​ሱም፥ “እኛ ከይ​ሁዳ ቤተ ልሔም ወደ ተራ​ራ​ማው ወደ ኤፍ​ሬም ሀገር ማዶ እና​ል​ፋ​ለን፤ እኔ ከዚያ ነኝ፤ ወደ ይሁዳ ቤተ ልሔ​ምም ሄጄ ነበር፥ አሁ​ንም ወደ ቤቴ እሄ​ዳ​ለሁ፤ በቤ​ቱም የሚ​ያ​ሳ​ድ​ረኝ አጣሁ፤


የተ​ገ​ደ​ለ​ች​ውም ሴት ባል ሌዋ​ዊዉ እን​ዲህ ብሎ መለ​ሰ​ላ​ቸው፥ “እኔና ዕቅ​ብቴ በዚያ ለማ​ደር ወደ ብን​ያም ሀገር ወደ ገባ​ዖን መጣን።


跟着我们:

广告


广告