Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 19:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 በዚ​ያም ዘመን ለእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ አል​ነ​በ​ራ​ቸ​ውም። በተ​ራ​ራ​ማ​ውም በኤ​ፍ​ሬም ሀገር ማዶ የተ​ቀ​መጠ አንድ ሌዋዊ ሰው ነበረ፤ ከይ​ሁዳ ቤተ ልሔ​ምም ዕቅ​ብት አገባ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 በዚያ ዘመን በእስራኤል ንጉሥ አልነበረም። በዚሁ ጊዜም በኰረብታማው በኤፍሬም አገር የሚኖር አንድ ሌዋዊ ከይሁዳ ምድር ከቤተ ልሔም አንዲቱን ሴት ቁባት አድርጎ ወሰዳት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 በዚያን ዘመን በእስራኤል ንጉሥ አልነበረም፤ በዚሁ ጊዜም በኰረብታማው በኤፍሬም አገር የሚኖር አንድ ሌዋዊ ከይሁዳ ምድር ከቤተልሔም አንዲቱን ሴት ቁባት አድርጎ ወሰዳት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 በእስራኤል ገና ንጉሥ ባልነበረበት ጊዜ በኮረብታማው በኤፍሬም አገር ራቅ ብሎ በሚገኝ ስፍራ የሚኖር አንድ ሌዋዊ ነበረ፤ ይህ ሰው በይሁዳ ግዛት ከምትገኘው ከቤተልሔም አንዲት ልጃገረድ ቊባት ወስዶ ነበር፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 በዚያም ዘመን በእስራኤል ዘንድ ንጉሥ በሌለበት ጊዜ በተራራማው በኤፍሬም አገር ማዶ የተቀመጠ ሌዋዊ ነበረ፥ ከቤተ ልሔምም ይሁዳ ቁባት አገባ።

参见章节 复制




መሳፍንት 19:1
29 交叉引用  

ሬሕማ የሚ​ሉ​አት ዕቅ​ብቱ ደግሞ ጥባ​ህን፥ ቤካን፥ ጠኮ​ንና ሜካን ወለ​ደች።


አብ​ር​ሃ​ምም ለቁ​ባ​ቶቹ ልጆች ሀብ​ትን ሰጣ​ቸው፤ እር​ሱም ገና በሕ​ይ​ወቱ ሳለ ከልጁ ከይ​ስ​ሐቅ ለይቶ ወደ ምሥ​ራቅ ሀገር ሰደ​ዳ​ቸው።


ራሔ​ልም ሞተች፤ ወደ ኤፍ​ራ​ታም በም​ት​ወ​ስድ መን​ገድ ተቀ​በ​ረች፤ እር​ስ​ዋም ቤተ ልሔም ናት።


ለአ​ቤ​ሴ​ሎ​ምም በሰ​ገ​ነት ላይ ድን​ኳን ተከ​ሉ​ለት፤ አቤ​ሴ​ሎ​ምም በእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ፊት ወደ አባቱ ቁባ​ቶች ገባ።


ኢዮ​አ​ብም ወደ ንጉሡ ወደ ቤት ገብቶ እን​ዲህ አለ፥ “ዛሬ ነፍ​ስ​ህ​ንና የወ​ን​ዶ​ች​ንና የሴ​ቶች ልጆ​ች​ህን ነፍስ፥ የሚ​ስ​ቶ​ች​ህ​ንና የቁ​ባ​ቶ​ች​ህን ነፍስ ያዳ​ኑ​ትን የአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ች​ህን ሁሉ ፊት በዚች ቀን አሳ​ፍ​ረ​ሃል።


ዳዊ​ትም ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ ቤቱ መጣ፤ ንጉ​ሡም ቤቱን ሊጠ​ብቁ የተ​ዋ​ቸ​ውን ዐሥ​ሩን ቁባ​ቶች ወስዶ ለጠ​ባቂ ሰጣ​ቸው፤ ቀለ​ብም ሰጣ​ቸው፤ ነገር ግን ወደ እነ​ርሱ አል​ገ​ባም፤ በቤ​ትም ተዘ​ግ​ተው እስ​ኪ​ሞቱ ድረስ መበ​ለ​ቶች ሆነው ተቀ​መጡ።


ለሳ​ኦ​ልም የኢ​ዮ​ሄል ልጅ ሩጻፋ የተ​ባ​ለች ዕቅ​ብት ነበ​ረ​ችው፤ ኢያ​ቡ​ስ​ቴም አበ​ኔ​ርን፥ “ወደ አባቴ ዕቅ​ብት ለምን ገባህ?” አለው።


ዳዊ​ትም ከኬ​ብ​ሮን ከመጣ በኋላ እንደ ገና ቁባ​ቶ​ቹ​ንና ሚስ​ቶ​ቹን ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ወሰደ፤ ለዳ​ዊ​ትም ደግሞ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆች ተወ​ለ​ዱ​ለት።


ለእ​ር​ሱም ሰባት መቶ ሚስ​ቶ​ችና ሦስት መቶ ቁባ​ቶች ነበ​ሩት።


ስማ​ቸ​ውም ይህ ነበረ፤ በተ​ራ​ራ​ማው ሀገር በኤ​ፍ​ሬም የሖር ልጅ ቢዖር፥


ሮብ​ዓ​ምም ከሚ​ስ​ቶ​ቹና ከቁ​ባ​ቶቹ ሁሉ ይልቅ የአ​ቤ​ሴ​ሎ​ምን ልጅ መዓ​ካን ወደደ፤ ዐሥራ ስም​ን​ትም ሚስ​ቶ​ችና ስድሳ ቁባ​ቶች ነበ​ሩት፤ ሃያ ስም​ንት ወን​ዶ​ችና ስድሳ ሴቶች ልጆ​ች​ንም ወለደ።


እግዚአብሔር የሕይወትን መንፈስ አንድ አድርጎ ጠብቆልን የለምን? እርሱም የሚፈልገው ምንድር ነው? ዘር አይደለምን? ስለዚህ መንፈሳችሁን ጠብቁ፥ ማንም የልጅነት ሚስቱን አያታልል።


በተ​ራ​ራ​ማ​ውም በኤ​ፍ​ሬም ሀገር በገ​ዓስ ተራራ በሰ​ሜን ባለ​ችው በር​ስቱ ዳርቻ በተ​ም​ና​ሴራ ቀበ​ሩት። በዚ​ያም ከግ​ብፅ በወጡ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘ​ዘው የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች በገ​ል​ገላ የገ​ረ​ዘ​ባ​ቸ​ውን የድ​ን​ጋይ ባል​ጩ​ቶ​ችን እር​ሱን በቀ​በ​ሩ​በት መቃ​ብር ከእ​ርሱ ጋር ቀበሩ፤ እስከ ዛሬም ድረስ በዚያ አሉ።


የአ​ሮ​ንም ልጅ ሊቀ ካህ​ናቱ አል​ዓ​ዛር ሞተ፤ በተ​ራ​ራ​ማ​ውም በኤ​ፍ​ሬም ሀገር ለልጁ ለፊ​ን​ሐስ በተ​ሰ​ጠ​ችው በጊ​ብ​ዓት መሬት ቀበ​ሩት።


ከእ​ር​ሱም በኋላ የቤተ ልሔሙ ሐሴ​ቦን እስ​ራ​ኤ​ልን ገዛ።


በተ​ራ​ራ​ማ​ውም በኤ​ፍ​ሬም ሀገር ሚካ የተ​ባለ አንድ ሰው ነበረ።


በዚ​ያም ዘመን በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ንጉሥ አል​ነ​በ​ረም፤ ሰውም ሁሉ በፊቱ መል​ካም መስሎ የታ​የ​ውን ያደ​ርግ ነበር።


በይ​ሁዳ ቤተ ልሔ​ምም ከይ​ሁዳ ወገን የሆነ አንድ ጐል​ማሳ ነበረ፤ እር​ሱም ሌዋዊ ነበረ፤ በዚ​ያም ይቀ​መጥ ነበር።


ይህም ሰው በአ​ገ​ኘው ስፍራ ይኖር ዘንድ ከይ​ሁዳ ከተማ ከቤተ ልሔም ሄደ፤ በዚ​ያም ያድር ዘንድ ወደ ተራ​ራ​ማው ወደ ኤፍ​ሬም ሀገር ወደ ሚካ ቤት ደረሰ።


በዚ​ያም ዘመን በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ንጉሥ አል​ነ​በ​ረም። እስ​ከ​ዚ​ያም ቀን ድረስ በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ዶች መካ​ከል ርስት አል​ደ​ረ​ሳ​ቸ​ውም ነበ​ርና በዚያ ዘመን የዳን ነገድ የሚ​ቀ​መ​ጡ​ባት ርስት ይሹ ነበር።


ከዚ​ያም ወደ ተራ​ራ​ማው ወደ ኤፍ​ሬም አገር አለፉ እስከ ሚካም ቤት ደረሱ።


እነ​ሆም አንድ ሽማ​ግሌ ከእ​ር​ሻው ሥራ ወደ ማታ መጣ፤ ይህም ሰው ከተ​ራ​ራ​ማው ከኤ​ፍ​ሬም ሀገር ነበረ፤ በገ​ባ​ዖ​ንም በእ​ን​ግ​ድ​ነት ተቀ​ምጦ ነበር፤ የዚያ ሀገር ሰዎች ግን የብ​ን​ያም ልጆች ነበሩ።


ዕቅ​ብ​ቱም ተጣ​ላ​ችው፤ ትታ​ውም ወደ አባቷ ቤት ወደ ይሁዳ ቤተ ልሔም ሄደች፤ በዚ​ያም አራት ወር ተቀ​መ​ጠች።


በዚ​ያም ዘመን በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ንጉሥ አል​ነ​በ​ረም፤ ሰው ሁሉ በፊቱ መል​ካም መስሎ የታ​የ​ውን ያደ​ርግ ነበር።


ከዚ​ህም በኋላ ወደ እስ​ራ​ኤል ምድር በደ​ረሰ ጊዜ በተ​ራ​ራ​ማው በኤ​ፍ​ራም ሀገር ቀንደ መለ​ከት ነፋ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ከእ​ርሱ ጋር ከተ​ራ​ራ​ማው ሀገር ወረዱ፤ እር​ሱም በፊ​ታ​ቸው ሄደ።


跟着我们:

广告


广告