Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 18:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 በሚካ ቤትም በነ​በሩ ጊዜ የሌ​ዋ​ዊ​ዉን የጐ​ል​ማ​ሳ​ውን ድምፅ ዐወቁ፤ ወደ እር​ሱም ቀር​በው፥ “ወደ​ዚህ ማን አመ​ጣህ? በዚ​ህስ የም​ታ​ደ​ር​ገው ምን​ድን ነው? በዚ​ህስ ምን አለህ?” አሉት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 በሚካ ቤት አጠገብ እንደ ደረሱም የወጣቱን ሌዋዊ ድምፅ ዐወቁ፤ ስለዚህ ወደዚያ ጐራ ብለው፣ “ወደዚህ ያመጣህ ማን ነው? እዚህ ምን ትሠራለህ? የመጣኸውስ ለምንድን ነው?” ሲሉ ጠየቁት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 በሚካ ቤት አጠገብ እንደ ደረሱም የወጣቱን ሌዋዊ ድምፅ ዐወቁ፤ ስለዚህ ወደዚያ ጐራ ብለው፥ “ወደዚህ ያመጣህ ማን ነው? እዚህ ምን ትሠራለህ? የመጣኸውስ ለምንድን ነው?”። ሲሉ ጠየቁት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 እዚያም በነበሩበት ጊዜ ወጣቱን ሌዋዊ በአነጋገሩ ሁኔታ ከየት እንደ ሆነ ለይተው ዐወቁት፤ ወደ እርሱም ቀርበው “እዚህ ምን ትሠራለህ፤ ወደዚህ ያመጣህስ ማነው?” ሲሉ ጠየቁት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 በሚካ ቤት አጠገብም በነበሩ ጊዜ የሌዋዊውን የጕልማሳውን ድምፅ አወቁ፥ ወደ እርሱም ቀርበው፦ ወደዚህ ማን አመጣህ? በዚህስ የምታደርገው ምንድር ነው? በዚህስ ምን አለህ? አሉት።

参见章节 复制




መሳፍንት 18:3
6 交叉引用  

ያዕ​ቆ​ብም ወደ አባቱ ወደ ይስ​ሐቅ ቀረበ፤ ዳሰ​ሰ​ውም፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “ይህ ድምፅ የያ​ዕ​ቆብ ድምፅ ነው፥ እጆች ግን የዔ​ሳው እጆች ናቸው” አለው።


መቃ​ብር በዚያ ያስ​ወ​ቀ​ርህ፥ ከፍ ባለው ስፍራ መቃ​ብር ያሠ​ራህ፥ በድ​ን​ጋ​ይም ውስጥ ለራ​ስህ መኖ​ርያ ያሳ​ነ​ጽህ ወደ​ዚህ ለምን መጣህ? ለም​ንስ በዚህ ተደ​ፋ​ፈ​ርህ?


ጥቂትም ቈይተው በዚያ ቆመው የነበሩ ቀርበው ጴጥሮስን “አነጋገርህ ይገልጥሃልና፥ በእውነት አንተ ደግሞ ከእነርሱ ወገን ነህ፤” አሉት።


እነ​ር​ሱም፥ “አሁን ሺቦ​ሌት በሉ” አሉ​አ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም አጥ​ር​ተው መና​ገር አል​ቻ​ሉ​ምና፥ “ሲቦ​ሌት” አሉ፤ ይዘ​ውም በዮ​ር​ዳ​ኖስ መሸ​ጋ​ገ​ርያ አረ​ዱ​አ​ቸው፤ በዚ​ያም ጊዜ ከኤ​ፍ​ሬም አርባ ሁለት ሺህ ሰዎች ወደቁ።


የዳ​ንም ልጆች ከወ​ገ​ና​ቸው አም​ስት ጽኑ​ዓን ሰዎች ምድ​ሪ​ቱን እን​ዲ​ሰ​ል​ሉና እን​ዲ​መ​ረ​ምሩ፥ “ሂዱ ምድ​ሪ​ቱ​ንም ሰልሉ” ብለው ከሶ​ራ​ሕና ከኢ​ስ​ታ​ሔል ላኩ። እነ​ዚ​ያም ወደ ተራ​ራ​ማዉ ወደ ኤፍ​ሬም ሀገር ወደ ሚካ ቤት መጥ​ተው በዚያ አደሩ።


እር​ሱም፥ “ሚካ እን​ዲህ እን​ዲህ አደ​ረ​ገ​ልኝ፤ ቀጠ​ረ​ኝም፤ እኔም ካህን ሆን​ሁ​ለት” አላ​ቸው።


跟着我们:

广告


广告