Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 18:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ምድ​ሪ​ቱ​ንም ሊሰ​ልሉ ሄደው የነ​በ​ሩት አም​ስቱ ሰዎች መጥ​ተው ወደ​ዚያ ገቡ፤ የተ​ቀ​ረ​ፀ​ው​ንም ምስል ኤፉ​ዱ​ንም፥ ተራ​ፊ​ሙ​ንም ቀልጦ የተ​ሠ​ራ​ውን ምስ​ልም ወሰዱ፤ ካህ​ኑም የጦር ዕቃ ከታ​ጠ​ቁት ከስ​ድ​ስት መቶ ሰዎች ጋር በደ​ጃፉ አጠ​ገብ ቆሞ ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ካህኑ ለጦርነት ከተዘጋጁት ስድስት መቶ ሰዎች ጋራ በቅጥሩ በር ላይ ቆሞ ሳለ፣ ምድሪቱን ለመሰለል መጥተው የነበሩትን ዐምስት ሰዎች ወደ ቤቱ ውስጥ በመግባት የተቀረጸውን ምስልና ኤፉዱን፣ ተራፊሙንና ቀልጦ የተሠራውን ምስል ወሰዱ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ካህኑ ለጦርነት ከተዘጋጁት ስድስት መቶ ሰዎች ጋር በቅጥሩ በር ላይ ቆሞ ሳለ፥ ምድሪቱን ለመሰለል መጥተው የነበሩትን አምስት ሰዎች ወደ ቤቱ ውስጥ በመግባት የተቀረጸውን ምስልና ኤፉዱን፥ ተራፊሙንና ቀልጦ የተሠራውን ምስል ወሰዱ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 አምስቱም ሰላዮች በቀጥታ ወደ ሚካ ቤት ገብተው ያንን በብር የተለበጠ የእንጨት ጣዖትና ሌሎቹንም ጣዖቶች ኤፉዱንም ጭምር ወሰዱ፤ ይህም በሚሆንበት ጊዜ ካህኑ የጦር መሣሪያ ከታጠቁት ስድስት መቶ ሰዎች ጋር በቅጽር በሩ አጠገብ ቆሞ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ምድሪቱንም ሊሰልሉ ሄደው የነበሩት አምስቱ ሰዎች ወጥተው ወደዚያ ገቡ፥ የተቀረጸውን ምስል ኤፉዱንም ተራፊሙንም ቀልጦ የተሠራውን ምስልም ወሰዱ፥ ካህኑም የጦር ዕቃ ከታጠቁት ከስድስት መቶ ሰዎች ጋር በደጃፉ አጠገብ ቆሞ ነበር።

参见章节 复制




መሳፍንት 18:17
19 交叉引用  

ላባ ግን በጎ​ቹን ለመ​ሸ​ለት ሄዶ ነበር፤ ራሔ​ልም የአ​ባ​ቷን ጣዖ​ቶች ሰረ​ቀች።


አሁ​ንም የአ​ባ​ት​ህን ቤት ከና​ፈ​ቅህ ሂድ፤ ነገር ግን አም​ላ​ኮ​ቼን ለምን ሰረ​ቅህ?”


የሠ​ሩ​ት​ንም ጥጃ ወስዶ በእ​ሳት አቀ​ለ​ጠው፤ ፈጨው፤ አደ​ቀ​ቀ​ውም፤ በው​ኃም ላይ በተ​ነው፤ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች አጠ​ጣ​ቸው።


የሚ​ሠ​ሩ​አ​ቸ​ውም በከ​ንቱ ይሠ​ሩ​አ​ቸ​ዋል።


በጫ​ን​ቃ​ቸው ላይ ተሸ​ክ​መ​ውት ይሄ​ዳሉ፤ በስ​ፍ​ራ​ውም በአ​ኖ​ሩት ጊዜ በዚያ ይቆ​ማል፤ ከስ​ፍ​ራ​ውም ፈቀቅ አይ​ልም፤ ሰውም ወደ እርሱ ቢጮህ አይ​ሰ​ማ​ውም፤ ከክ​ፉም አያ​ድ​ነ​ውም።


የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ምዋ​ር​ቱን ያም​ዋ​ርት ዘንድ፥ በት​ሩን ያነሣ ዘንድ፥ ጣዖ​ቱ​ንም ይጠ​ይቅ ዘንድ በሁ​ለት መን​ገ​ዶች ራስ ላይ ይቆ​ማል።


የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ያለ ንጉ​ሥና ያለ አለቃ፥ ያለ መሥ​ዋ​ዕ​ትና ያለ ምሥ​ዋዕ፤ ያለ ካህ​ንና ያለ ራእይ፤ ያለ ኤፉ​ድና ያለ ተራ​ፊም ብዙ ወራት ይቀ​መ​ጣ​ሉና፤


የተቀረጹትን ምስሎችህንና ሐውልቶችህን ከመካከልህ አጠፋለሁ፥ ለእጅህም ሥራ ከእንግዲህ ወዲህ አትሰግድም፥


የሌ​ሳን ምድር ሊሰ​ልሉ ሄደው የነ​በ​ሩት አም​ስቱ ሰዎ​ችም ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ውን፥ “በእ​ነ​ዚህ ቤቶች ውስጥ ኢፉ​ድና ተራ​ፊም፥ የተ​ቀ​ረፀ ምስ​ልና ቀልጦ የተ​ሠራ ምስ​ልም እን​ዳሉ ታው​ቃ​ላ​ች​ሁን?፤ አሁ​ንም የም​ታ​ደ​ር​ጉ​ትን ዕወቁ” ብለው ተና​ገ​ሩ​አ​ቸው።


የጦር ዕቃ የታ​ጠ​ቁት፥ ከዳን ልጆ​ችም የሆ​ኑት ስድ​ስቱ መቶ ሰዎች በደ​ጃፉ አጠ​ገብ ቆመው ነበር።


እነ​ዚ​ህም ሰዎች ወደ ሚካ ቤት ገብ​ተው የተ​ቀ​ረ​ፀ​ውን ምስል፥ ኤፉ​ዱ​ንም፥ ተራ​ፊ​ሙ​ንም፥ ቀልጦ የተ​ሠ​ራ​ውን ምስ​ልም ወሰዱ፤ ካህ​ኑም፥ “ምን ታደ​ር​ጋ​ላ​ችሁ?” አላ​ቸው።


የዳ​ንም ልጆች ከወ​ገ​ና​ቸው አም​ስት ጽኑ​ዓን ሰዎች ምድ​ሪ​ቱን እን​ዲ​ሰ​ል​ሉና እን​ዲ​መ​ረ​ምሩ፥ “ሂዱ ምድ​ሪ​ቱ​ንም ሰልሉ” ብለው ከሶ​ራ​ሕና ከኢ​ስ​ታ​ሔል ላኩ። እነ​ዚ​ያም ወደ ተራ​ራ​ማዉ ወደ ኤፍ​ሬም ሀገር ወደ ሚካ ቤት መጥ​ተው በዚያ አደሩ።


ኢዮ​አ​ስም በእ​ርሱ ላይ የተ​ነ​ሡ​በ​ትን ሁሉ፥ “ለበ​ዓል እና​ንተ ዛሬ ትበ​ቀ​ሉ​ለ​ታ​ላ​ች​ሁን? ወይስ የበ​ደ​ለ​ውን ትገ​ድ​ሉ​ለት ዘንድ የም​ታ​ድ​ኑት እና​ንተ ናች​ሁን? እርሱ አም​ላክ ከሆ​ነስ የበ​ደ​ለው እስከ ነገ ድረስ ይሙት። መሠ​ዊ​ያ​ዉ​ንም ያፈ​ረ​ሰ​ውን እርሱ ይበ​ቀ​ለው” አላ​ቸው።


ሜል​ኮ​ልም ተራ​ፊ​ምን ወስዳ በአ​ልጋ ላይ አኖ​ረ​ችው፤ በራ​ስ​ጌ​ውም ጕን​ጕን የፍ​የል ጠጕር አደ​ረ​ገች፤ በል​ብ​ስም ከደ​ነ​ችው።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ታቦት ተማ​ረ​ከች፤ ሁለ​ቱም የዔሊ ልጆች አፍ​ኒ​ንና ፊን​ሐስ ሞቱ።


跟着我们:

广告


广告