መሳፍንት 18:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)14 የሌሳን ምድር ሊሰልሉ ሄደው የነበሩት አምስቱ ሰዎችም ወንድሞቻቸውን፥ “በእነዚህ ቤቶች ውስጥ ኢፉድና ተራፊም፥ የተቀረፀ ምስልና ቀልጦ የተሠራ ምስልም እንዳሉ ታውቃላችሁን?፤ አሁንም የምታደርጉትን ዕወቁ” ብለው ተናገሩአቸው። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም14 የላይሽን ምድር ሰልለው የነበሩት ዐምስቱ ሰዎች ለወንድሞቻቸው፣ “ከእነዚሁ ቤቶች በአንዱ ኤፉድ፣ ተራፊም፣ የተቀረጸ ምስልና ቀልጦ የተሠራ ጣዖት እንዳለ ታውቃላችሁን? እንግዲህ ምን ማድረግ እንዳለባችሁ ዕወቁበት” አሏቸው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)14 የላይሽን ምድር ሰልለው የነበሩት አምስቱ ሰዎች ለወንድሞቻቸው፥ “ከእነዚሁ ቤቶች በአንዱ ኤፉድ፥ ተራፊም፥ የተቀረጸ ምስልና ቀልጦ የተሠራ ጣዖት እንዳለ ታውቃላችሁን? እንግዲህ ምን ማድረግ እንዳለባችሁ ዕወቁበት” አሏቸው። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም14 በላዪሽ ዙሪያ ያለውን አገር ሊያጠኑ ተልከው የነበሩት አምስት ሰዎች ለጓደኞቻቸው “በዚህ ስፍራ ከነዚህ ቤቶች በአንዱ ውስጥ በብር የተለበጠ የእንጨት ጣዖት እንዳለ ታውቃላችሁን? ሌሎች ጣዖቶች አንድ ኤፉድም በተጨማሪ አለ፤ ታዲያ ምን ማድረግ የሚገባን ይመስላችኋል?” አሉአቸው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)14 የሌሳን ምድር ሊሰልሉ ሄደው የነበሩት አምስቱ ሰዎችም ወንድሞቻቸውን፦ በእነዚህ ቤቶች ውስጥ ኤፉድና ተራፊም፥ የተቀረጸ ምስልና ቀልጦ የተሠራ ምስልም እንዳሉ ታውቃላችሁን? አሁንም የምታደርጉትን ምከሩ ብለው ተናገሩአቸው። 参见章节 |