Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 17:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 እና​ቱ​ንም፥ “ከአ​ንቺ ዘንድ የተ​ሰ​ረ​ቀው፥ የረ​ገ​ም​ሽ​በ​ትም፥ በጆ​ሮ​ዬም የተ​ና​ገ​ር​ሽ​በት አንድ ሺህ አንድ መቶ ብር እነሆ፥ በእኔ ዘንድ አለ፤ እኔም ወስ​ጄው ነበር” አላት። እና​ቱም፥ “ልጄ ሆይ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይባ​ር​ክህ” አለ​ችው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 እናቱን፣ “አንድ ሺሕ አንድ መቶ ሰቅል ብር ተሰርቆብሽ፣ የሰረቀውን ሰው ስትራገሚ ሰምቼሽ ነበር፤ ብሩ ከእኔ ዘንድ ይገኛል፤ የወሰድሁት እኔ ነኝ” አላት። ከዚያም እናቱ፣ “ልጄ፤ እግዚአብሔር ይባርክህ” አለችው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 እናቱን፥ “አንድ ሺህ አንድ መቶ ሰቅል ብር ተሰርቆብሽ፥ የሰረቀውን ሰው ስትራገሚ ሰምቼሽ ነበር፤ ብሩ ከእኔ ዘንድ ይገኛል፤ የወሰድሁት እኔ ነኝ” አላት። ከዚያም እናቱ፥ “ልጄ፤ ጌታ ይባርክህ” አለችው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 እርሱም አንድ ቀን እናቱን እንዲህ አላት፤ “አንድ ሰው አንድ ሺህ አንድ መቶ ጥሬ ብር በሰረቀሽ ጊዜ ያን የሰረቀሽን ሰው ስትረግሚው ሰምቼሽ ነበር፤ እነሆ ያ ብር በእኔ እጅ ነው፤ እርሱንም የወሰድኩ እኔ ነበርኩ።” እናቱም “ልጄ! እግዚአብሔር ይባርክህ!” አለችው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 እናቱንም፦ ከአንቺ ዘንድ የተወሰደው፥ የረገምሽበትም፥ በጆሮዬም የተናገርሽበት አንድ ሺህ አንድ መቶ ብር፥ እነሆ፥ በእኔ ዘንድ አለ፥ እኔም ወስጄዋለሁ አላት። እናቱም፦ ልጄ ሆይ፥ እግዚአብሔር ይባርክህ አለችው።

参见章节 复制




መሳፍንት 17:2
21 交叉引用  

አብ​ራ​ም​ንም ባረ​ከው፤ “አብ​ራም ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን ለፈ​ጠረ ለል​ዑል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ባ​ረከ ነው፤


እነ​ር​ሱ​ንም ተቈ​ጣ​ኋ​ቸው፤ ረገ​ም​ኋ​ቸ​ውም፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ዐያ​ሌ​ዎ​ቹን መታሁ፤ ጠጕ​ራ​ቸ​ው​ንም ነጨሁ፤ እን​ዲ​ህም ብዬ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አማ​ል​ኋ​ቸው፥ “ሴቶች ልጆ​ቻ​ች​ሁን ለወ​ን​ዶች ልጆ​ቻ​ቸው አት​ስጡ፤ ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም ለወ​ን​ዶች ልጆ​ቻ​ችሁ አት​ው​ሰዱ።


አንተ የሠ​ራ​ኸ​ውን እነሆ፥ እነ​ርሱ አፍ​ር​ሰ​ዋ​ልና፤ ጻድቅ ግን ምን አደ​ረገ?


“የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የአ​ም​ላ​ክ​ህን ስም በከ​ንቱ አት​ጥራ፤ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስሙን በከ​ንቱ የሚ​ጠ​ራ​ውን ከበ​ደል አያ​ነ​ጻ​ው​ምና።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሥራ በቸ​ልታ የሚ​ያ​ደ​ርግ ርጉም ይሁን፤ ሰይ​ፉ​ንም ከደም የሚ​ከ​ለ​ክል ርጉም ይሁን።


በዚያን ጊዜ “ሰውየውን አላውቀውም፤” ብሎ ራሱን ሊረግምና ሊምል ጀመረ። ወዲያውም ዶሮ ጮኸ።


በሥጋ ዘመ​ዶ​ችና ወን​ድ​ሞች ስለ​ሚ​ሆኑ እኔ ከክ​ር​ስ​ቶስ እለይ ዘንድ እጸ​ል​ያ​ለሁ።


ጌታ​ች​ንን ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን የማ​ይ​ወ​ደው የተ​ለየ ይሁን፤ ጌታ​ችን ይመ​ጣል።


“አባ​ቱን ወይም እና​ቱን የሚ​ያ​ቃ​ልል ርጉም ይሁን፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ አሜን ይላሉ።


ሰላም የሚለው ሰው በክፉ ሥራው ይካፈላልና።


በተ​ራ​ራ​ማ​ውም በኤ​ፍ​ሬም ሀገር ሚካ የተ​ባለ አንድ ሰው ነበረ።


አን​ዱን ሺህ አንድ መቶ ብርም ለእ​ናቱ መለ​ሰ​ላት፤ እና​ቱም፥ “ይህን ብር የተ​ቀ​ረፀ ምስ​ልና ቀልጦ የተ​ሠራ ምስል አድ​ርጌ ከእጄ ስለ ልጄ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እቀ​ድ​ሰ​ዋ​ለሁ፤ አሁ​ንም ለአ​ንተ እመ​ል​ሰ​ዋ​ለሁ” አለች።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ አለ፥ “ሜሮ​ዝን ርገሙ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ርዳታ አል​መ​ጡ​ምና፥ በኀ​ያ​ላን መካ​ከል ወደ እርሱ ርዳታ አል​መ​ጡ​ምና፥ በቤ​ቶ​ችዋ ያሉ​ትን ሰዎች ፈጽ​ማ​ችሁ ርገሙ።”


ቦዔዝም አላት፦ ልጄ ሆይ፥ በእግዚአብሔር የተባረክሽ ሁኚ፣ ባለጠጋም ድሀም ብለሽ ጐበዛዝትን አልተከተልሽምና ከፊተኛው ይልቅ በመጨረሻው ጊዜ ቸርነት አድርገሻል።


ሳኦ​ልም በዚያ ቀን ትልቅ በደል ፈጸመ፤ “ጠላ​ቶቼን እስ​ክ​በ​ቀል እስከ ማታ ድረስ መብል የሚ​በላ ሰው ርጉም ይሁን” ብሎ ሕዝ​ቡን አም​ሎ​አ​ቸው ነበ​ርና። ሕዝ​ቡም ሁሉ እህል አል​ቀ​መ​ሱም። ሀገ​ሩም ሁሉ ምሳ አል​በ​ላም።


ከሕ​ዝ​ቡም አንድ ሰው መልሶ፥ “አባ​ትህ፦ ዛሬ መብል የሚ​በላ ሰው ርጉም ይሁን ብሎ ሕዝ​ቡን መሐላ አም​ሎ​አ​ቸ​ዋል” አለው፤ ሕዝ​ቡም ደከሙ።


ሳሙ​ኤ​ልም ወደ ሳኦል መጣ፤ ሳኦ​ልም፥ “አንተ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ባ​ረ​ክህ ሁን፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዘ​ዘ​ውን ሁሉ ፈጽ​ሜ​አ​ለሁ” አለው።


ሳኦ​ልም አለ፥ “እና​ንተ ስለ እኔ አዝ​ና​ች​ኋ​ልና በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የተ​ባ​ረ​ካ​ችሁ ሁኑ፤


አሁ​ንም ጌታዬ ንጉሥ ሆይ! የእ​ኔን የአ​ገ​ል​ጋ​ይ​ህን ቃል ስማ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእኔ ላይ አስ​ነ​ሥ​ቶህ እን​ደ​ሆነ፥ ቍር​ባ​ን​ህን ይቀ​በል፤ የሰው ልጆች ግን ቢሆኑ፦ ሂድ ሌሎ​ችን አማ​ል​ክት አም​ልክ ብለው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ርስት ላይ እን​ዳ​ል​ቀ​መጥ ዛሬ ጥለ​ው​ኛ​ልና በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ርጉ​ማን ይሁኑ።


跟着我们:

广告


广告