Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 16:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 ሶም​ሶ​ንም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኸ፥ እን​ዲ​ህም አለ፥ “አቤቱ ጌታዬ ሆይ! አስ​በኝ፤ ጌታዬ ሆይ! አንድ ጊዜ አበ​ር​ታኝ፤ እን​ግ​ዲህ ስለ ሁለቱ ዐይ​ኖቼ ፋንታ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን አን​ዲት በቀ​ልን እበ​ቀ​ላ​ለሁ።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 ሳምሶንም ወደ እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ጸለየ፤ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ አስበኝ። አምላክ ሆይ፤ እባክህን አንድ ጊዜ ብቻ ብርታት ስጠኝና ስለ ጠፉት ዐይኖቼ ፍልስጥኤማውያንን አንዴ ልበቀላቸው።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 ሳምሶንም ወደ ጌታ እንዲህ ሲል ጸለየ፤ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ አስበኝ፤ አምላክ ሆይ፤ እባክህን አንድ ጊዜ ብቻ ብርታት ስጠኝና ስለ ጠፉት ዐይኖቼ ፍልስጥኤማውያንን አንዴ ልበቀላቸው።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 ከዚህ በኋላ ሶምሶን “ልዑል እግዚአብሔር ሆይ! እባክህ አስበኝ፤ አምላኬ ሆይ! እባክህ ኀይል ስጠኝና ፍልስጥኤማውያን ዐይኖቼን ስላወጡ አንድ ጊዜ ብቻ እንድበቀላቸው አድርገኝ!” ብሎ ጸለየ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 ሶምሶንም፦ ስለ ሁለቱ ዓይኖቼ ፍልስጥኤማውያንን አሁን እንድበቀል፥ እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፥ እባክህ፥ አስበኝ፥ አምላክ ሆይ፥ ይህን አንድ ጊዜ ብቻ፥ እባክህ፥ አበርታኝ ብሎ እግዚአብሔርን ጠራ።

参见章节 复制




መሳፍንት 16:28
19 交叉引用  

አም​ላ​ካ​ችን ሆይ፥ አንተ አት​ፈ​ር​ድ​ባ​ቸ​ው​ምን? ይህን የመ​ጣ​ብ​ንን ታላቅ ወገን መቃ​ወም እን​ችል ዘንድ ኀይል የለ​ንም፤ የም​ና​ደ​ር​ግ​ባ​ቸ​ው​ንም አና​ው​ቅም፤ ነገር ግን ዐይ​ኖ​ቻ​ችን ወደ አንተ ናቸው።”


ልጆ​ቻ​ቸው በጐ​ል​ማ​ስ​ነ​ታ​ቸው እንደ አዲስ ተክል የሆኑ፥ ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ውም እንደ እል​ፍኝ ያማ​ሩና ያጌጡ፤


አቤቱ፥ ከን​ፈ​ሮ​ችን ክፈት፥ አፌም ምስ​ጋ​ና​ህን ያወ​ራል።


አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እው​ነ​ተኛ እንደ ሆነ ይና​ገ​ራሉ፥ በእ​ር​ሱም ዘንድ ዐመፃ የለም።


አቤቱ! አንተ ታው​ቃ​ለህ፤ አስ​በኝ፤ ጐብ​ኘ​ኝም፤ ከሚ​ያ​ሳ​ድ​ዱ​ኝም አድ​ነኝ እንጂ፥ አት​ታ​ገ​ሣ​ቸው፤ ስለ አንተ እንደ ሰደ​ቡኝ አስብ።


እነሆ ራሴ ወደ ታች ወደ ተራ​ሮች መሠ​ረት ወረደ፤ ከጥ​ንት ጀምሮ መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎ​ችዋ ወደ ተዘጉ ምድር ወረ​ድሁ፤ አቤቱ ፈጣ​ሪዬ! ሕይ​ወቴ ጥፋት ሳያ​ገ​ኛት ወዳ​ንተ ትውጣ።


የናስ አንጥረኛው እስክንድሮስ እጅግ ከፋብኝ፤ ጌታ እንደ ሥራው ይመልስለታል።


እን​ግ​ዲህ ምን እላ​ለሁ? ስለ ጌዴ​ዎን፥ ስለ ባርቅ፥ ስለ ሶም​ሶን፥ ስለ ዮፍ​ታሔ፥ ስለ ዳዊት፥ ስለ ሳሙ​ኤ​ልና ስለ ሌሎች ነቢ​ያት እነ​ግ​ራ​ችሁ ዘንድ ጊዜዬ አጭር ነውና።


በታላቅ ድምፅም እየጮኹ “ቅዱስና እውነተኛ ጌታ ሆይ! እስከ መቼ ድረስ አትፈርድም? ደማችንንስ በምድር በሚኖሩት ላይ እስከ መቼ አትበቀልም?” አሉ።


እር​ሱም እጅግ ተጠ​ምቶ ነበ​ርና፥ “አንተ ይህ​ችን ታላቅ ማዳን በባ​ሪ​ያህ እጅ ሰጥ​ተ​ሃል፤ አሁ​ንም በጥም እሞ​ታ​ለሁ፤ ባል​ተ​ገ​ረ​ዙ​ትም እጅ እወ​ድ​ቃ​ለሁ” ብሎ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኸ።


በቤ​ትም ውስጥ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ሞል​ተ​ው​በት ነበር፤ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤም መሳ​ፍ​ን​ትም ሁሉ በዚያ ነበሩ፤ በቤ​ቱም ሰገ​ነት ላይ ሶም​ሶን ሲጫ​ወት የሚ​ያዩ ሦስት ሺህ የሚ​ያ​ህሉ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ነበሩ።


ሶም​ሶ​ንም ቤቱ ተደ​ግ​ፎ​ባ​ቸው የነ​በ​ሩ​ትን ሁለ​ቱን መካ​ከ​ለ​ኞች ምሰ​ሶ​ዎች ያዘ፤ አን​ዱን በቀኝ እጁ፥ አን​ዱ​ንም በግራ እጁ ይዞ ገፋ​ቸው።


አቤቱ ጠላ​ቶ​ችህ ሁሉ እን​ዲሁ ይጥፉ፤ ወዳ​ጆ​ችህ ግን ፀሐይ በኀ​ይሉ በወጣ ጊዜ እን​ደ​ሚ​ሆን፤ እን​ዲሁ ይሁኑ። ምድ​ሪ​ቱም አርባ ዓመት ያህል ዐረ​ፈች።


跟着我们:

广告


广告