መሳፍንት 16:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)26 ሶምሶንም የሚመራውን ብላቴና፥ “ቤቱን የደገፉትን ምሰሶዎች እደገፍባቸው ዘንድ እባክህ አስይዘኝ” አለው፥ ብላቴናውም እንዳለው አደረገለት። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም26 ሳምሶን እጁን ይዞ የሚመራውን ልጅ፣ “ቤተ ጣዖቱን ደግፈው ወደ ያዙት ምሰሶዎች አስጠጋኝና ልደገፋቸው” አለው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)26 ሳምሶን እጁን ይዞ የሚመራውን ልጅ፥ “ቤተ ጣዖቱ ደግፈው ወደ ያዙት ምሰሶዎች አስጠጋኝና ልደገፋቸው” አለው። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም26 ሶምሶንም እጁን ይዞ የሚመራውን ልጅ፥ “ሕንጻውን ደግፈው የያዙትን ምሰሶዎች አስጨብጠኝና እነርሱን ተደግፌ ልቁም” አለው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)26 ሶምሶንም እጁን የያዘውን ብላቴና፦ ቤቱን የደገፉትን ምሰሶች እጠጋባቸው ዘንድ፥ እባክህ፥ አስይዘኝ አለው። 参见章节 |