Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 16:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 ከዚ​ህም በኋላ ልባ​ቸ​ውን ደስ ባለው ጊዜ፥ “በፊ​ታ​ችን እን​ዲ​ጫ​ወት ሶም​ሶ​ንን ከእ​ስር ቤት ጥሩት” አሉ። ሶም​ሶ​ን​ንም ከእ​ስር ቤት ጠሩት፤ በፊ​ታ​ቸ​ውም ተጫ​ወተ፤ ተዘ​ባ​በ​ቱ​በ​ትም፤ በም​ሰ​ሶና በም​ሰ​ሶም መካ​ከል አቆ​ሙት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 እጅግ ደስ ባላቸው ጊዜ፣ “እንዲያዝናናን ሳምሶንን አምጡት” አሉ፤ ስለዚህ ሳምሶንን ከእስር ቤት ጠርተው አስመጡት፤ በፊታቸውም ተጫወተ። በምሰሶዎቹ መካከል ባቆሙት ጊዜ፣

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 እጅግ ደስ ባላቸው ጊዜ፥ “እንዲያዝናናን ሳምሶንን አምጡት” አሉ፤ ስለዚህ ሳምሶንን ከእስር ቤት ጠርተው አስመጡት፤ በፊታቸውም ተጫወተ። በምሶሶዎቹ መካከል ባቆሙት ጊዜ፥

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 ልባቸውንም ደስ ባለው ጊዜ እንዲጫወትልን ሶምሶንን ጥሩት አሉ ሶምሶንንም ከግዞት ቤት ጠሩት፤ በፊታቸውም ተጫወተ፤ በምሰሶና በምሰሶ መካከል አቆሙት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 ልባቸውንም ደስ ባለው ጊዜ፦ በፊታችን እንዲጫወት ሶምሶንን ጥሩት አሉ። ሶምሶንንም ከግዞት ቤት ጠሩት፥ በፊታቸውም ተጫወተ፥ ተዘባበቱበትም፥ በምሰሶና በምሰሶም መካከል አቆሙት።

参见章节 复制




መሳፍንት 16:25
23 交叉引用  

አቤ​ሴ​ሎ​ምም እንደ ንጉሥ ግብዣ ያለ ግብዣ አደ​ረገ፤ አቤ​ሴ​ሎ​ምም አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹን፥ “አም​ኖን የወ​ይን ጠጅ ጠጥቶ ልቡን ደስ ባለው ጊዜ እዩ፦ አም​ኖ​ንን ግደሉ ባል​ኋ​ችሁ ጊዜ ግደ​ሉት። አት​ፍ​ሩም፤ ያዘ​ዝ​ኋ​ች​ሁም እኔ ነኝና በርቱ፤ ጽኑም” ብሎ አዘ​ዛ​ቸው።


የጾም አዋ​ጅም ነገሩ፤ ናቡ​ቴ​ንም በሕ​ዝቡ ፊት በከ​ፍ​ተኛ ቦታ አስ​ቀ​መ​ጡት።


እነ​ሆም፥ በዓ​ልን፥ ደስ​ታ​ንና ሐሴ​ትን አደ​ረ​ጋ​ችሁ፤ በሬ​ዎ​ች​ንና በጎ​ች​ንም አረ​ዳ​ችሁ፤ “ነገ እን​ሞ​ታ​ለን፤ እን​ብላ፤ እን​ጠ​ጣም፤” እያ​ላ​ችሁ ሥጋን በላ​ችሁ፤ ወይ​ን​ንም ጠጣ​ችሁ።


ከእሾህም አክሊል ጐንጕነው በራሱ ላይ፥ በቀኝ እጁም መቃ አኖሩ፤ በፊቱም ተንበርክከው “የአይሁድ ንጉሥ ሆይ! ሰላም ለአንተ ይሁን፤” እያሉ ዘበቱበት፤


የገ​ረ​ፉ​አ​ቸው፥ የዘ​በ​ቱ​ባ​ቸ​ውና ያሠ​ሩ​አ​ቸው ወደ ወህኒ ያገ​ቡ​አ​ቸ​ውም አሉ።


ሕዝ​ቡም ሁሉ ባዩት ጊዜ፥ “ምድ​ራ​ች​ንን ያጠ​ፋ​ውን፥ ከእ​ኛም ብዙ ሰው የገ​ደ​ለ​ውን ጠላ​ታ​ች​ንን አም​ላ​ካ​ችን በእ​ጃ​ችን አሳ​ልፎ ሰጠን እያሉ አም​ላ​ካ​ቸ​ውን አመ​ሰ​ገኑ።


ሶም​ሶ​ንም የሚ​መ​ራ​ውን ብላ​ቴና፥ “ቤቱን የደ​ገ​ፉ​ትን ምሰ​ሶ​ዎች እደ​ገ​ፍ​ባ​ቸው ዘንድ እባ​ክህ አስ​ይ​ዘኝ” አለው፥ ብላ​ቴ​ና​ውም እን​ዳ​ለው አደ​ረ​ገ​ለት።


ካህ​ኑም በልቡ ደስ አለው፤ ኤፉ​ዱ​ንም፥ ተራ​ፊ​ሙ​ንም፥ የተ​ቀ​ረ​ፀ​ው​ንም ምስል፥ ቀልጦ የተ​ሠ​ራ​ው​ንም ምስል ወሰደ፤ በሕ​ዝ​ቡም መካ​ከል ገባ።


ሁለ​ቱም በአ​ንድ ላይ ተቀ​መጡ፤ በሉም፤ ጠጡም፤ የብ​ላ​ቴ​ና​ዪ​ቱም አባት ሰው​ዬ​ውን፥ “ዛሬ ደግሞ ከዚህ እደር ልብ​ህ​ንም ደስ ይበ​ለው” አለው።


ሰው​ዬ​ውም ከዕ​ቅ​ብ​ቱና ከብ​ላ​ቴ​ናው ጋር ለመ​ሄድ ተነሣ፤ የብ​ላ​ቴ​ና​ዪቱ አባት አማ​ቱም፥ “እነሆ፥ መሽ​ት​ዋል፤ ፀሐ​ዩም ሊጠ​ልቅ ደር​ሷል፤ ዛሬም እዚህ እደር፤ በዚ​ህም ተቀ​መጥ፤ ልብ​ህም ደስ ይበ​ለው፤ በጥ​ዋ​ትም መን​ገ​ዳ​ች​ሁን ትገ​ሠ​ግ​ሣ​ላ​ችሁ፤ ወደ ቤት​ህም ትገ​ባ​ለህ” አለው።


ወደ እር​ሻ​ውም ወጡ፤ ወይ​ና​ቸ​ው​ንም ለቀሙ፤ ጠመ​ቁ​ትም፤ የደ​ስ​ታም በዓል አደ​ረጉ፤ ወደ አም​ላ​ካ​ቸ​ውም ቤት ገቡ፤ በሉም፤ ጠጡም፤ አቤ​ሜ​ሌ​ክ​ንም ረገ​ሙት።


跟着我们:

广告


广告