Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 16:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ደሊ​ላም፥ “ ‘አንተ እወ​ድ​ድ​ሻ​ለሁ’ እን​ዴት ትለ​ኛ​ለህ? ልብህ ከእኔ ጋር አይ​ደ​ለም፤ ስታ​ታ​ል​ለኝ ይህ ሦስ​ተኛ ጊዜህ ነው፥ ታላቅ ኀይ​ል​ህም በምን እንደ ሆነ አል​ነ​ገ​ር​ኸ​ኝም” አለ​ችው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ከዚያም፣ “ሳታምነኝ እንዴት ‘እወድድሻለሁ’ ትለኛለህ? ስታታልለኝና የኀይልህንም ታላቅነት ምስጢር ስትደብቀኝ ይህ ሦስተኛ ጊዜህ ነው” አለችው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ከዚያም፥ “ሳታምነኝ እንዴት ‘እወድሻለሁ’ ትለኛለህ? ስታታልለኝና የኃይልህንም ታላቅነት ምስጢር ስትደብቀኝ ይህ ሦስተኛ ጊዜህ ነው” አለችው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ስለዚህ እርስዋ “ልብህ ከእኔ ጋር ሳይሆን እንዴት እወድሻለሁ ትለኛለህ? ሦስት ጊዜ አታለልከኝ፤ እስከ አሁንም ይህን ሁሉ ብርታት ያገኘኸው ከምን እንደ ሆነ አልነገርከኝም” አለችው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 እርስዋም፦ አንተ፦ እወድድሻለሁ እንዴት ትለኛለህ፥ ልብህ ከእኔ ጋር አይደለም? ስታታልለኝ ይህ ሦስተኛ ጊዜህ ነው፥ ታላቅ ኃይልህም በምን እንደ ሆነ አልነገርኸኝም አለችው።

参见章节 复制




መሳፍንት 16:15
18 交叉引用  

ያዕ​ቆ​ብም ስለ ራሔል ሰባት ዓመት ተገዛ፤ እር​ስ​ዋ​ንም ይወ​ድ​ዳት ስለ​ነ​በረ በእ​ርሱ ዘንድ ጥቂት ቀን ሆነ​ለት።


አቤ​ሴ​ሎ​ምም ኩሲን፥ “ስለ ወዳ​ጅህ ያደ​ረ​ግ​ኸው ቸር​ነት ይህ ነውን? ከወ​ዳ​ጅህ ጋር ያል​ሄ​ድህ ስለ ምን​ድን ነው?” አለው።


እን​ዲ​ህም ቃል አራት ጊዜ ላኩ​ብኝ፤ እኔም እንደ ፊተ​ኛው ቃል መለ​ስ​ሁ​ላ​ቸው።


ከቀናች መንገድ እንዳያርቁህ፥ እውነትንም ከማወቅ የተለየህ እንዳያደርጉህ፤ ልጄ ሆይ፥ በሕፃንነትህ ትምህርትን የምታስተው፥ ክፉ ምክር አታግኝህ፤


ልጄ ሆይ፥ ልብህን ስጠኝ፥ ዐይኖችህም መንገዴን ይጠብቁ።


“ከወ​ደ​ዳ​ች​ሁ​ኝስ ትእ​ዛ​ዜን ጠብቁ።


የም​ት​ወ​ዱኝ ብት​ሆኑ ትእ​ዛ​ዜን ጠብቁ፤ እኔ የአ​ባ​ቴን ትእ​ዛዝ እንደ ጠበ​ቅሁ፥ በፍ​ቅ​ሩም እን​ደ​ም​ኖር እና​ን​ተም ትእ​ዛ​ዜን ብት​ጠ​ብቁ በፍ​ቅሬ ትኖ​ራ​ላ​ችሁ።


አም​ላ​ክ​ህ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በፍ​ጹም ልብህ፥ በፍ​ጹ​ምም ነፍ​ስህ፥ በፍ​ጹ​ምም ኀይ​ልህ ውደድ።


ትእዛዛቱን ልንጠብቅ የእግዚአብሔር ፍቅር ይህ ነውና፤ ትእዛዛቱም ከባዶች አይደሉም።


የሶ​ም​ሶ​ንም ሚስት በፊቱ እያ​ለ​ቀ​ሰ​ች​በት፥ “ጠል​ተ​ኸ​ኛል፤ ከቶም አት​ወ​ድ​ደ​ኝም፤ ለሕ​ዝቤ ልጆች የነ​ገ​ር​ኸ​ውን እን​ቆ​ቅ​ል​ሽ​ህን አል​ነ​ገ​ር​ኸ​ኝ​ምና” አለ​ችው። እር​ሱም፥ “እነሆ፥ ለአ​ባ​ቴና ለእ​ናቴ አል​ነ​ገ​ር​ኋ​ቸ​ውም፤ ለአ​ንቺ እነ​ግ​ር​ሻ​ለ​ሁን?” አላት።


ደሊ​ላም አስ​ተ​ኛ​ችው፤ የራ​ሱ​ንም ጠጕር ሰባ​ቱን ጕን​ጕን ከድር ጋር ጐነ​ጐ​ነ​ችው፤ በግ​ድ​ግ​ዳም ላይ በች​ካል ቸከ​ለ​ቻ​ቸው፥ “ሶም​ሶን ሆይ! ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን መጡ​ብህ” አለ​ችው። ከእ​ን​ቅ​ል​ፉም ነቃ፥ ችካ​ሉ​ንም ከነ​ቈ​ን​ዳ​ላው ከግ​ድ​ግ​ዳው ነቀለ፤ ኀይ​ሉም አል​ታ​ወ​ቀም።


ከዚ​ህም በኋላ ሌሊ​ቱን ሁሉ በነ​ገር በዘ​በ​ዘ​በ​ች​ውና በአ​ደ​ከ​መ​ችው ጊዜ፥ ልሙት እስ​ኪል ድረስ ተበ​ሳጨ።


跟着我们:

广告


广告