መሳፍንት 15:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)19 እግዚአብሔርም የዚያችን የአህያ መንጋጋ አጥንት ስንጥቃት ከፈተ፤ ከእርስዋም ውኃ ወጣ፤ እርሱም ጠጣ፤ ነፍሱም ተመለሰች፤ ከውኃ ጥሙም ዐረፈ። ስለዚህም የዚያ ቦታ ስም እስከ ዛሬ ድረስ “ነቅዐ አጽመ መንሰክ” ተብሎ ተጠራ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም19 እግዚአብሔርም በሌሒ ዐለት ሰነጠቀለት፤ ከዚያም ውሃ ወጣ፤ ሳምሶንም ያን ሲጠጣ በረታ፤ መንፈሱም ታደሰ። ስለዚህ ያ ምንጭ ዓይንሀቆሬ ተባለ፤ እስከ ዛሬም ድረስ በዚያው በሌሒ ይገኛል። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)19 እግዚአብሔርም በሌሒ ዐለት ሰነጠቀለት፤ ከዚያም ውኃ ወጣ፤ ሳምሶንም ያን ሲጠጣ በረታ፤ መንፈሱም ታደሰ። ስለዚህ ያ ምንጭ ዓይንሀቆሬሸ ተባለ፤ እስከ ዛሬም ድረስ በዚያው በሌሒ ይገኛል። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም19 እግዚአብሔር በሌሂ ያለው ጐድጓዳ ቦታ ከፈተለት፤ ከእርሱም ውሃ ወጣ፤ በጠጣም ጊዜ መንፈሱ ተመልሶለት ተጠናከረ፤ ስለዚህም ያ ቦታ “ዐይን ሃቆሬ” የተባለ። እርሱም እስከ ዛሬ ድረስ በሌሂ ይገኛል። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)19 እግዚአብሔርም በሌሒ ያለውን አዘቅት ሰነጠቀ፥ ከእርሱም ውኃ ወጣ፥ እርሱም ጠጣ፥ ነፍሱም ተመለሰች፥ ተጠናከረም። ስለዚህም የዚያን ቦታ ስም ዓይንሀቆሬ ብሎ ጠራው፥ ይህም እስከ ዛሬ ድረስ በሌሒ አለ። 参见章节 |