Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 14:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ሰባ​ቱ​ንም የበ​ዓል ቀን አለ​ቀ​ሰ​ች​በት፤ እር​ስ​ዋም ነዝ​ን​ዛ​ዋ​ለ​ችና በሰ​ባ​ተ​ኛው ቀን ነገ​ራት። ለሕ​ዝ​ብ​ዋም ልጆች ነገ​ረ​ቻ​ቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ሚስቱም በሰርጉ በዓል ሰባት ቀን ሙሉ እያለቀሰች ጨቀጨቀችው፤ አጥብቃ ስለ ነዘነዘችውም በመጨረሻ በሰባተኛው ቀን ነገራት፤ እርሷም በበኩሏ የዕንቈቅልሹን ፍች ለሕዝቧ ነገረች።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ሚስቱም በሰርጉ በዓል ሰባት ቀን ሙሉ እያለቀሰች ጨቀጨቀችው፤ አጥብቃ ስለ ነዘነዘችውም በመጨረሻ በሰባተኛው ቀን ነገራት፤ እርሷም በበኩሏ የእንቈቅልሹን ፍች ለሕዝቧ ነገረች።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ከዚህም የተነሣ እርስዋ በሠርጉ በዓል ሰባት ቀን ሙሉ አለቀሰች፤ አጥብቃም ስለ ነዘነዘችው የእንቆቅልሹን ፍች በሰባተኛው ቀን ነገራት፤ እርስዋም ሄዳ ለፍልስጥኤማውያኑ ነገረቻቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ሰባቱንም የበዓል ቀን በፊቱ አለቀሰች፥ እርስዋም ነዝንዛዋለችና በሰባተኛው ቀን ነገራት። ትርጓሜውንም ለሕዝብዋ ልጆች ነገረች።

参见章节 复制




መሳፍንት 14:17
13 交叉引用  

ሴቲ​ቱም ዛፉ ለመ​ብ​ላት ያማረ እን​ደ​ሆነ፥ ለዐ​ይ​ንም ለማ​የት እን​ደ​ሚ​ያ​ስ​ጐ​መጅ፥ መል​ካ​ም​ንም እን​ደ​ሚ​ያ​ሳ​ውቅ ባየች ጊዜ፥ ከፍ​ሬው ወሰ​ደ​ችና በላች፤ ለባ​ል​ዋም ደግሞ ሰጠ​ችው፤ እር​ሱም ከእ​ር​ስዋ ጋር በላ።


ብዙ ወራ​ትም ካለፈ በኋላ ሚስቱ እን​ዲህ አለ​ችው፥ “እስከ መቼ ትታ​ገ​ሣ​ለህ? 9 ‘ሀ’ ዳግ​መ​ኛም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጥቂት ወራት ደጅ እጠ​ና​ዋ​ለሁ፤ ዳግ​መ​ኛም መከ​ራ​ውን እታ​ገ​ሠ​ዋ​ለሁ፤ የቀ​ድ​ሞው ኑሬ​ዬ​ንም ተስፋ አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ ትላ​ለ​ህን? 9 ‘ለ’ እን​ደ​ዚ​ህስ እን​ዳ​ትል ከዚህ ዓለም እነሆ ስም አጠ​ራ​ርህ ጠፋ፤ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆቼም ሞቱ፥ ማኅ​ፀ​ኔም በምጥ ተጨ​ነቀ፥ በከ​ን​ቱም ደከ​ምሁ። 9 ‘ሐ’ አን​ተም በመ​ግ​ልና በትል ትኖ​ራ​ለህ፤ ሌሊ​ቱ​ንም ሁሉ ትዛ​ብ​ራ​ለህ። 9 ‘መ’ እኔ ግን እየ​ዞ​ርሁ እቀ​ላ​ው​ጣ​ለሁ። ከአ​ንዱ መን​ደር ወደ አንዱ መን​ደር፥ ከአ​ንዱ ቤትም ወደ አንዱ ቤት እሄ​ዳ​ለሁ፤ ከድ​ካ​ሜና በእኔ ላይ ካለ ችግ​ሬም ዐርፍ ዘንድ ፀሐይ እስ​ኪ​ገባ ድረስ እጠ​ብ​ቃ​ለሁ፤ ነገር ግን አሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስደ​ብና ሙት።”


በብዙ ጨዋታዋ እንዲስት ታደርገዋለች፤ በከንፈርዋ ወጥመድም ትጐትተዋለች።


“ምላ​ሳ​ቸ​ውን ለሐ​ሰት እንደ ቀስት ገተሩ፤ በም​ድ​ርም በረቱ፤ ነገር ግን ለእ​ው​ነት አይ​ደ​ለም፤ ከክ​ፋት ወደ ክፋት ይሄ​ዳ​ሉና፥ እኔ​ንም አላ​ወ​ቁ​ምና፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ባልንጀራን አትመኑ፥ በወዳጅም አትታመኑ፥ የአፍህን ደጅ በብብትህ ከምትተኛው ጠብቅ።


ወዳጁ ስለ​ሆነ ሊሰ​ጠው ባይ​ነሣ እንኳ እን​ዳ​ይ​ዘ​በ​ዝ​በው ተነ​ሥቶ የወ​ደ​ደ​ውን ያህል ይሰ​ጠ​ዋል።


የሶ​ም​ሶ​ንም ሚስት በፊቱ እያ​ለ​ቀ​ሰ​ች​በት፥ “ጠል​ተ​ኸ​ኛል፤ ከቶም አት​ወ​ድ​ደ​ኝም፤ ለሕ​ዝቤ ልጆች የነ​ገ​ር​ኸ​ውን እን​ቆ​ቅ​ል​ሽ​ህን አል​ነ​ገ​ር​ኸ​ኝ​ምና” አለ​ችው። እር​ሱም፥ “እነሆ፥ ለአ​ባ​ቴና ለእ​ናቴ አል​ነ​ገ​ር​ኋ​ቸ​ውም፤ ለአ​ንቺ እነ​ግ​ር​ሻ​ለ​ሁን?” አላት።


በሰ​ባ​ተ​ኛ​ዪ​ቱም ቀን ፀሐይ ሳት​ገባ የከ​ተ​ማ​ዪቱ ሰዎች፥ “ከማር የሚ​ጣ​ፍጥ ምን​ድን ነው? ከአ​ን​በ​ሳስ የሚ​በ​ረታ ማን ነው?” አሉት። ሶም​ሶ​ንም፥ “በጥ​ጃዬ ባላ​ረ​ሳ​ችሁ ኑሮ የእ​ን​ቆ​ቅ​ል​ሼን ትር​ጓሜ ባላ​ወ​ቃ​ች​ሁም ነበር” አላ​ቸው።


ደሊ​ላም ሶም​ሶ​ንን፥ “እስከ አሁን ድረስ አታ​ለ​ል​ኸኝ፤ የነ​ገ​ር​ኸ​ኝም ሐሰት ነው፤ የም​ት​ታ​ሰ​ር​በት ምን እን​ደ​ሆነ ንገ​ረኝ” አለ​ችው። እር​ሱም፥ “የራ​ሴን ጠጕር ሰባ​ቱን ጕን​ጕን ከድር ጋር ብት​ጐ​ነ​ጕ​ኚው፥ በግ​ድ​ግ​ዳም ላይ በች​ካል ብት​ቸ​ክ​ዪው፥ ከሰ​ዎች እንደ አንዱ እደ​ክ​ማ​ለሁ፥” አላት።


ከዚ​ህም በኋላ ሌሊ​ቱን ሁሉ በነ​ገር በዘ​በ​ዘ​በ​ች​ውና በአ​ደ​ከ​መ​ችው ጊዜ፥ ልሙት እስ​ኪል ድረስ ተበ​ሳጨ።


ደሊ​ላም ሶም​ሶ​ንን፥ “ታላቅ ኀይ​ልህ በምን እንደ ሆነ፥ በም​ንስ ብት​ታ​ሰር እን​ደ​ምትዋ​ረድ እባ​ክህ ንገ​ረኝ” አለ​ችው።


跟着我们:

广告


广告