መሳፍንት 14:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)15 ከዚህ በኋላ በአራተኛው ቀን የሶምሶንን ሚስት፥ “እንቆቅልሹን እንዲነግርሽ ባልሽን አባብይው፤ አለዚያም አንቺንና የአባትሽን ቤት በእሳት እናቃጥላለን፤ ወይስ ወደዚህ የጠራችሁን ልታደኸዩን ነውን?” አሉአት። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም15 በአራተኛው ቀን የሳምሶንን ሚስት፣ “የዕንቈቅልሹን ፍች እንዲነግረን ባልሽን እስኪ አግባቢልን፤ አለዚያ አንቺንም የአባትሽንም ቤተ ሰብ በእሳት እናቃጥላችኋለን፤ ጠርታችሁ የጋበዛችሁን ልትዘርፉን ነው?” አሏት። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)15 በአራተኛው ቀን የሳምሶንን ሚስት፥ “የእንቈቅልሹን ፍች እንዲነግረን ባልሽን እስቲ አግባቢልን፤ ያለዚያ አንቺንም የአባትሽንም ቤተሰብ በእሳት እናቃጥላችኋለን፤ ጠርታችሁ የጋበዛችሁን ልትዘርፉን ነው እንዴ?” አሏት። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም15 በአራተኛው ቀን የሶምሶንን ሚስት እንዲህ አሉአት፤ “ባልሽን አግባብተሽ የእንቆቅልሹን ፍች እንዲነግረን አድርጊ፤ ይህን ካላደረግሽ ግን የአባትሽን ቤት በእሳት አያይዘን አንቺንም በውስጡ በመጨመር እናቃጥልሻለን፤ ለካስ እናንተ ሁለታችሁም ወደ ግብዣችሁ የጠራችሁን ልትዘርፉን ኖሮአልን?” 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)15 በአራተኛውም ቀን የሶምሶንን ሚስት፦ እንቈቅልሹን እንዲነግረን ባልሽን ሸንግዪው፥ አለዚያም አንቺንና የአባትሽን ቤት በእሳት እናቃጥላለን፥ ወደዚህ ጠራችሁን ልትገፉን ነውን? አሉአት። 参见章节 |