Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 13:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ማኑ​ሄም ሚስ​ቱን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አይ​ተ​ና​ልና ሞትን እን​ሞ​ታ​ለን” አላት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ማኑሄም ሚስቱን፣ “እግዚአብሔርን ስላየን ያለ ጥርጥር እንሞታለን” አላት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ሚስቱንም፥ “እግዚአብሔርን ስላየን ያለ ጥርጥር እንሞታለን” አላት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ማኑሄ ሚስቱን “እግዚአብሔርን ስላየን በእርግጥ እንሞታለን!” አላት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ማኑሄም ሚስቱን፦ እግዚአብሔርን አይተናልና ሞት እንሞታለን አላት።

参见章节 复制




መሳፍንት 13:22
11 交叉引用  

በዚ​ያም ስፍራ ባረ​ከው። ያዕ​ቆ​ብም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፊት ለፊት አየሁ፤ ሰው​ነ​ቴም ዳነች” ሲል የዚ​ያን ቦታ ስም “ራእየ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር” ብሎ ጠራው።


የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የቆ​መ​በ​ትን ቦታ አዩ፤ ከእ​ግ​ሩም በታች እንደ ሰማይ መልክ የሚ​ያ​በራ፥ እንደ ብሩህ ሰን​ፔር ድን​ጋይ የሚ​መ​ስል ወለል ነበረ።


ሙሴም፥ አሮ​ንም፥ ናዳ​ብም፥ አብ​ዩ​ድም፥ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰባ ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ወጡ፤


ደግ​ሞም፥ “እኔ የአ​ባ​ቶ​ችህ አም​ላክ፥ የአ​ብ​ር​ሃም አም​ላክ፥ የይ​ስ​ሐ​ቅም አም​ላክ፥ የያ​ዕ​ቆ​ብም አም​ላክ ነኝ” አለው። ሙሴም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያይ ዘንድ ፈር​ቶ​አ​ልና ፊቱን መለሰ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “ሰው አይ​ቶኝ አይ​ድ​ን​ምና ፊቴን ማየት አይ​ቻ​ል​ህም” አለ።


እኔም፥ “ከን​ፈ​ሮች የረ​ከ​ሱ​ብኝ ሰው በመ​ሆኔ፥ ከን​ፈ​ሮ​ቻ​ቸው በረ​ከ​ሱ​ባ​ቸው ሕዝብ መካ​ከል በመ​ቀ​መጤ ዐይ​ኖች የሠ​ራ​ዊ​ትን ጌታ ንጉ​ሡን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስለ አዩ ጠፍ​ቻ​ለ​ሁና ወዮ​ልኝ!” አልሁ።


በአ​ባቱ ዕቅፍ ያለ አንድ ልጅ እርሱ ገለ​ጠ​ልን እንጂ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንስ ከቶ ያየው የለም።


የላ​ከኝ አብም ስለ እኔ መስ​ክ​ሮ​አል፤ ከሆ​ነም ጀምሮ ቃሉን አል​ሰ​ማ​ች​ሁም፤ መል​ኩ​ንም አላ​ያ​ች​ሁም።


ዛሬ እንደ ሆነው ሁሉ ከግ​ብፅ ከአ​ንተ የጸ​ኑ​ትን ታላ​ላ​ቆ​ቹን አሕ​ዛብ በፊ​ትህ እን​ዲ​ያ​ወጣ፥ አን​ተ​ንም እን​ዲ​ያ​ገ​ባህ፥ ምድ​ራ​ቸ​ው​ንም ርስት አድ​ርጎ እን​ዲ​ሰ​ጥህ፥


ከሥጋ ለባሽ ሁሉ እኛ እንደ ሰማን በእ​ሳት መካ​ከል ሆኖ ሲና​ገር የሕ​ያው አም​ላ​ክን ድምፅ ሰምቶ በሕ​ይ​ወት የኖረ ማን ነው?


ጌዴ​ዎ​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ እንደ ሆነ ዐወቀ። ጌዴ​ዎ​ንም፥ “አቤቱ! አም​ላኬ ሆይ! ወዮ​ልኝ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መል​አክ ፊት ለፊት አይ​ቻ​ለ​ሁና” አለ።


跟着我们:

广告


广告