መሳፍንት 13:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)16 የእግዚአብሔርም መልአክ ማኑሄን፥ “አንተ የግድ ብትለኝ እህልህን አልበላም፤ የሚቃጠለውንም መሥዋዕት ብታደርግ ለእግዚአብሔር አቅርበው” አለው። ማኑሄም የእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን አላወቀም ነበር። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም16 የእግዚአብሔርም መልአክ ማኑሄን፣ “የግድ ብታቈየኝ እንኳ የምታቀርበውን ማንኛውንም ምግብ አልበላም፤ ነገር ግን የሚቃጠል መሥዋዕት የምታዘጋጅ ከሆነ እርሱን ለእግዚአብሔር አቅርበው” አለው። የሚያነጋግረው የእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን አላወቀም ነበር። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)16 የጌታም መልአክ፥ “የግድ ብታቈየኝ እንኳ የምታቀርበውን ማንኛውንም ምግብ አልበላም፤ ነገር ግን የሚቃጠል መሥዋዕት የምታዘጋጅ ከሆነ እርሱን ለጌታ አቅርበው” አለው። የሚያነጋግረው የጌታ መልአክ መሆኑን አላወቀም ነበር። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም16 የእግዚአብሔርም መልአክ ማኑሄን “ምንም አንተ ብታቈየኝ ምግብህን አልበላም፤ የሚቃጠል መሥዋዕት ማዘጋጀት ብትፈልግ ግን ለእግዚአብሔር አቅርበው” አለው። ማኑሄ የእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን አላወቀም ነበር። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)16 የእግዚአብሔርም መልአክ ማኑሄን፦ አንተ የግድ ብትለኝ መብልህን አልበላም፥ የሚቃጠለውንም መሥዋዕት ማዘጋጀት ብትወድድ ለእግዚአብሔር አቅርበው አለው። ማኑሄም የእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን አላወቀም ነበር። 参见章节 |