Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 12:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 የገ​ለ​ዓድ ሰዎ​ችም ኤፍ​ሬም በሚ​ያ​ል​ፍ​በት በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ ደረ​ሱ​ባ​ቸው። ከዚህ በኋላ ከኤ​ፍ​ሬም ያመ​ለ​ጡት እን​ሻ​ገር ባሉ ጊዜ የገ​ለ​ዓድ ሰዎች፥ “በውኑ እና​ንተ ከኤ​ፍ​ሬም ወገን ናች​ሁን?” ቢሉ​አ​ቸው “አይ​ደ​ለ​ንም” አሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ገለዓዳውያን ወደ ኤፍሬም የሚያሻግሩትን የዮርዳኖስን መልካዎች ያዙ። ታዲያ አምልጦ የሚሸሽ አንድ ኤፍሬማዊ ለመሻገር በሚጠይቃቸው ጊዜ፣ የገለዓድ ሰዎች “አንተ ኤፍሬማዊ ነህ?” ብለው ይጠይቁታል፤ ያም ሰው፣ “አይደለሁም” ብሎ ከመለሰላቸው፣

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ገለዓዳውያን ወደ ኤፍሬም የሚያሻግሩትን የዮርዳኖስን መሻገሪያዎች ያዙ፤ ታድያ አምልጦ የሚሸሽ አንድ ኤፍሬማዊ ለመሻገር በሚጠይቃቸው ጊዜ፥ የገለዓድ ሰዎች “አንተ ኤፍሬማዊ ነህ?” ብለው ይጠይቁታል፤ ያም ሰው፥ “አይደለሁም” ብሎ ከመለሰላቸው፥

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 የኤፍሬም ሰዎች እንዳያመልጡ ለማድረግ ገለዓዳውያን የዮርዳኖስን መሻገሪያ ቦታዎች ሁሉ ዘግተው ያዙ፤ ለማምለጥ የሚሞክር ማንኛውም የኤፍሬም ሰው ለመሻገር ፈቃድ ቢጠይቅ ገለዓዳውያን “አንተ የኤፍሬም ሰው ነህን?” ብለው ይጠይቁት ነበር፤ “አይደለሁም!” ካለ፥

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ገለዓዳውያንም ኤፍሬም የሚያልፍበትን የዮርዳኖስን መሻገርያ ያዙባቸው፥ የሸሸም የኤፍሬም ሰው፦ ልለፍ ባለ ጊዜ፥ የገለዓድ ሰዎች፦ አንተ ኤፍሬማዊ ነህን? አሉት፥ እርሱም፦ አይደለሁም ቢል፥

参见章节 复制




መሳፍንት 12:5
9 交叉引用  

ከሳ​ሪራ ሀገር የሆነ የኤ​ፍ​ሬ​ማ​ዊው የና​ባ​ጥና ሳሩሃ የተ​ባ​ለች የመ​በ​ለት ልጅ ኢዮ​ር​ብ​ዓም የሰ​ሎ​ሞን አገ​ል​ጋይ ነበረ።


ሰዎ​ቹም ወደ ዮር​ዳ​ኖስ መሻ​ገ​ሪያ በሚ​ወ​ስ​ደው መን​ገድ ተከ​ተ​ሉ​አ​ቸው፤ በሩም ተቈ​ለፈ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በከ​ነ​ዓን ምድር ዳርቻ በዮ​ር​ዳ​ኖስ አጠ​ገብ ባለው በገ​ለ​ዓድ፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ባሉ​በት ወገን፥ የሮ​ቤል ልጆ​ችና የጋድ ልጆች የም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ መሠ​ዊያ እንደ ሠሩ ሰሙ።


ዮፍ​ታ​ሔም የገ​ለ​ዓ​ድን ሰዎች ሁሉ ሰበ​ሰበ፤ ከኤ​ፍ​ሬ​ምም ጋር ተዋጋ፤ ኤፍ​ሬ​ምም፥ “ገለ​ዓ​ዳ​ው​ያን ሆይ! እና​ንተ በኤ​ፍ​ሬ​ምና በም​ናሴ መካ​ከል የተ​ቀ​መ​ጣ​ችሁ ከኤ​ፍ​ሬም ሸሽ​ታ​ችሁ ነው” ስላሉ የገ​ለ​ዓድ ሰዎች ኤፍ​ሬ​ምን መቱ።


እነ​ር​ሱም፥ “አሁን ሺቦ​ሌት በሉ” አሉ​አ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም አጥ​ር​ተው መና​ገር አል​ቻ​ሉ​ምና፥ “ሲቦ​ሌት” አሉ፤ ይዘ​ውም በዮ​ር​ዳ​ኖስ መሸ​ጋ​ገ​ርያ አረ​ዱ​አ​ቸው፤ በዚ​ያም ጊዜ ከኤ​ፍ​ሬም አርባ ሁለት ሺህ ሰዎች ወደቁ።


በይ​ሁዳ ቤተ ልሔ​ምም ከይ​ሁዳ ወገን የሆነ አንድ ጐል​ማሳ ነበረ፤ እር​ሱም ሌዋዊ ነበረ፤ በዚ​ያም ይቀ​መጥ ነበር።


እር​ሱም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ ጠላ​ቶ​ቻ​ች​ንን ሞዓ​ባ​ው​ያ​ንን በእ​ጃ​ችን አሳ​ልፎ ሰጥ​ቶ​ና​ልና ተከ​ተ​ሉኝ” አላ​ቸው። ተከ​ት​ለ​ው​ትም ወረዱ፤ ወደ ሞዓ​ብም የሚ​ያ​ሻ​ግ​ረ​ውን የዮ​ር​ዳ​ኖ​ስን መሻ​ገ​ርያ ያዙ፤ ማንም ሰው እን​ዲ​ያ​ልፍ አል​ፈ​ቀ​ዱም።


ጌዴ​ዎ​ንም፥ “ምድ​ያ​ማ​ው​ያ​ንን ለመ​ግ​ጠም ውረዱ፥ እስከ ቤት​ባ​ራም ድረስ ያለ​ውን ውኃ፥ ዮር​ዳ​ኖ​ስ​ንም፥ ያዙ​ባ​ቸው” ብሎ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን በኤ​ፍ​ሬም ወዳ​ለው ተራ​ራማ ሀገር ሁሉ ላከ። የኤ​ፍ​ሬ​ምም ሰዎች ሁሉ ተሰ​ብ​ስ​በው እስከ ቤት​ባራ ድረስ ውኃ​ውን፥ ዮር​ዳ​ኖ​ስ​ንም ቀድ​መው ያዙ።


በተ​ራ​ራ​ማው በኤ​ፍ​ሬም ሀገር ከአ​ር​ማ​ቴም መሴፋ የሆነ አንድ ሰው ነበረ። ስሙም፥ የና​ሲብ ልጅ የቴቆ ልጅ፥ የኤ​ልዩ ልጅ ፥ የኢ​ያ​ር​ም​ያል ልጅ፥ ኤፍ​ራ​ታ​ዊው ሕል​ቃና ነበረ።


跟着我们:

广告


广告