Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 12:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ዮፍ​ታ​ሔም የገ​ለ​ዓ​ድን ሰዎች ሁሉ ሰበ​ሰበ፤ ከኤ​ፍ​ሬ​ምም ጋር ተዋጋ፤ ኤፍ​ሬ​ምም፥ “ገለ​ዓ​ዳ​ው​ያን ሆይ! እና​ንተ በኤ​ፍ​ሬ​ምና በም​ናሴ መካ​ከል የተ​ቀ​መ​ጣ​ችሁ ከኤ​ፍ​ሬም ሸሽ​ታ​ችሁ ነው” ስላሉ የገ​ለ​ዓድ ሰዎች ኤፍ​ሬ​ምን መቱ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ከዚያም ዮፍታሔ የገለዓድን ሰዎች አሰባስቦ ከኤፍሬም ጋራ ተዋጋ። ኤፍሬማውያን ገለዓዳውያንን፣ “እናንተ ገለዓዳውያን ከኤፍሬምና ከምናሴ የከዳችሁ ናችሁ” ይሏቸው ስለ ነበር በብርቱ መቷቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ከዚያም ዮፍታሔ የገለዓድን ሰዎች አሰባስቦ ከኤፍሬም ጋር ተዋጋ። ኤፍሬማውያን ገለዓዳውያንን፥ “እናንተ ገለዓዳውያን ከኤፍሬምና ከምናሴ የከዳችሁ ናችሁ” ይሏቸው ስለ ነበር በብርቱ መቷቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ከዚህ በኋላ ዮፍታሔ የገለዓድን ሰዎች አሰባስቦ በኤፍሬም ሰዎች ላይ አደጋ በመጣል ድል አደረጋቸው፤ የኤፍሬም ሰዎች “እናንተ በኤፍሬምና በምናሴ ግዛት ውስጥ የምትኖሩ ገለዓዳውያን ኤፍሬምን ከድታችሁ የመጣችሁ ናችሁ!” ይሉአቸው ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ዮፍታሔም የገለዓድን ሰዎች ሁሉ ሰበሰበ፥ ከኤፍሬምም ጋር ተዋጋ፥ ኤፍሬምም፦ ገለዓዳውያን ሆይ፥ እናንተ በኤፍሬምና በምናሴ መካከል የተቀመጣችሁት ከኤፍሬም ሸሽታችሁ ነው ስላሉ የገለዓድ ሰዎች ኤፍሬምን መቱ።

参见章节 复制




መሳፍንት 12:4
11 交叉引用  

በገ​ለ​ዓድ ቴስ​ባን የነ​በ​ረው ቴስ​ብ​ያ​ዊው ነቢዩ ኤል​ያስ አክ​ዓ​ብን፥ “በፊቱ የቆ​ም​ሁት የኀ​ያ​ላን አም​ላክ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ከአፌ ቃል በቀር በእ​ነ​ዚህ ዓመ​ታት ዝና​ብም ጠልም አይ​ወ​ር​ድም” አለው።


አም​ላ​ካ​ችን ሆይ፥ ተን​ቀ​ና​ልና ስማ፤ ስድ​ባ​ቸ​ውን በራ​ሳ​ቸው ላይ መል​ስ​ባ​ቸው፤ በም​ርኮ ሀገር ለብ​ዝ​በዛ አሳ​ል​ፈህ ስጣ​ቸው።


አም​ላ​ካ​ች​ንና መድ​ኀ​ኒ​ታ​ችን ሆይ፥ ርዳን፥ ስለ ስምህ ክብር አቤቱ፥ ታደ​ገን፥ ስለ ስም​ህም ኀጢ​አ​ታ​ች​ንን አስ​ተ​ስ​ር​ይ​ልን።


ኀጢአተኛ ሰው በከንፈሩ ኀጢአት ወደ ወጥመድ ይወድቃል፤ ጻድቅ ግን ከእርሱ ያመልጣል። አስፍቶ የሚመለከት ሰው ብዙ ምሕረትን ያገኛል። ድንገት በበር የሚገናኝ ግን ነፍሳትን ያስጨንቃል።


ቍጣ ጥበበኞችን ታጠፋለች፤ የለዘበ ቃል ቍጣን ይመልሳል፥ ሻካራ ቃል ግን ጠብን ያነሣሣል።


የገ​ለ​ዓ​ድም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ዮፍ​ታ​ሔን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ካ​ከ​ላ​ችን ምስ​ክር ይሁን፤ በር​ግጥ እንደ ቃልህ እና​ደ​ር​ጋ​ለን” አሉት።


የሚ​ያ​ድን እን​ደ​ሌ​ለም ባየሁ ጊዜ ሰው​ነ​ቴን በእጄ አሳ​ልፌ ለሞት በመ​ስ​ጠት ወደ አሞን ልጆች ተሻ​ገ​ርሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በፊቴ ጣላ​ቸው፤ ለም​ንስ ዛሬ ልት​ወ​ጉኝ ወደ እኔ መጣ​ችሁ?” አላ​ቸው።


የገ​ለ​ዓድ ሰዎ​ችም ኤፍ​ሬም በሚ​ያ​ል​ፍ​በት በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ ደረ​ሱ​ባ​ቸው። ከዚህ በኋላ ከኤ​ፍ​ሬም ያመ​ለ​ጡት እን​ሻ​ገር ባሉ ጊዜ የገ​ለ​ዓድ ሰዎች፥ “በውኑ እና​ንተ ከኤ​ፍ​ሬም ወገን ናች​ሁን?” ቢሉ​አ​ቸው “አይ​ደ​ለ​ንም” አሉ።


ናባ​ልም ተነ​ሥቶ ለዳ​ዊት ብላ​ቴ​ኖች መለ​ሰ​ላ​ቸው እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “ዳዊት ማን ነው? የእ​ሴ​ይስ ልጅ ማን ነው? እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው ከጌ​ቶ​ቻ​ቸው የኰ​በ​ለሉ አገ​ል​ጋ​ዮች ዛሬ ብዙ ናቸው።


跟着我们:

广告


广告