Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 12:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 የሚ​ያ​ድን እን​ደ​ሌ​ለም ባየሁ ጊዜ ሰው​ነ​ቴን በእጄ አሳ​ልፌ ለሞት በመ​ስ​ጠት ወደ አሞን ልጆች ተሻ​ገ​ርሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በፊቴ ጣላ​ቸው፤ ለም​ንስ ዛሬ ልት​ወ​ጉኝ ወደ እኔ መጣ​ችሁ?” አላ​ቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 እኔም እንደማትረዱኝ በተረዳሁ ጊዜ በሕይወቴ ቈርጬ አሞናውያንን ለመውጋት ተሻገርሁ፤ እግዚአብሔርም ድሉን ሰጠኝ። ታዲያ ዛሬ እኔን ለመውጋት የመጣችሁት ለምንድን ነው?”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 እኔም እንደማትረዱኝ በተረዳሁ ጊዜ በሕይወቴ ቈርጬ አሞናውያንን ለመውጋት ተሻገርሁ፤ ጌታም ድሉን ሰጠኝ፤ ታዲያ ዛሬ እኔን ለመውጋት የመጣችሁት ለምንድን ነው?”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 እናንተ እኔን ለመርዳት አለመፈለጋችሁን ባየሁ ጊዜ ለሕይወቴ ሳልሳሳ እነርሱን ለመውጋት ወሰኑን ተሻግሬ ሄድሁ፤ እግዚአብሔርም በእነርሱ ላይ ድልን አቀዳጀኝ። ታዲያ፥ አሁን እኔን ለመውጋት የተነሣችሁበት ምክንያት ምንድን ነው?”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 እንዳላዳናችሁኝም ባየሁ ጊዜ ነፍሴን በእጄ አድርጌ በአሞን ልጆች ላይ አለፍሁ፥ እግዚአብሔርም በእጄ አሳልፎ ሰጣቸው፥ ለምንስ ዛሬ ልትወጉኝ ወደ እኔ መጣችሁ? አላቸው።

参见章节 复制




መሳፍንት 12:3
11 交叉引用  

እነ​ሆም፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእኛ ላይ አለቃ ነው፤ መለ​ከ​ቱ​ንም የሚ​ነፉ ካህ​ናቱ ከእኛ ጋር ናቸው፤ በእ​ና​ን​ተም ላይ ይጮ​ኻሉ። የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሆይ፥ አይ​በ​ጃ​ች​ሁ​ምና ከአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ አም​ላክ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር አቷጉ።”


ሥጋ​ዬን በጥ​ርሴ እይ​ዛ​ለሁ፤ ሕይ​ወ​ቴ​ንም በእጄ አጥ​ብቄ አኖ​ራ​ታ​ለሁ።


ስለ እኔ ሰው​ነ​ታ​ቸ​ውን ለመ​ከራ አሳ​ል​ፈው ሰጥ​ተ​ዋ​ልና፤ የማ​መ​ሰ​ግ​ና​ቸ​ውም እኔ ብቻ አይ​ደ​ለ​ሁም፤ ከአ​ሕ​ዛብ ያመኑ ምእ​መ​ናን ሁሉ ያመ​ሰ​ግ​ኑ​አ​ቸ​ዋል እንጂ።


እነርሱም በበጉ ደም በምስክራቸውም ቃል ድል ነሡት፤ ነፍሳቸውንም እስከ ሞት ድረስ አልወደዱም።


እኔ አል​በ​ደ​ል​ሁ​ህም፤ አንተ ግን ከእኔ ጋር ትዋጋ ዘንድ ክፉ አታ​ድ​ር​ግ​ብኝ፤ ፈራጁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆ​ችና በአ​ሞን ልጆች መካ​ከል ዛሬ ይፍ​ረድ።”


ዮፍ​ታ​ሔም፥ “እኔና ሕዝቤ የተ​ገ​ፋን ነን፤ የአ​ሞን ልጆ​ችም በጽ​ኑዕ አሠ​ቃ​ዩን፤ በጠ​ራ​ና​ች​ሁም ጊዜ ከእ​ጃ​ቸው አላ​ዳ​ና​ች​ሁ​ንም።


ዮፍ​ታ​ሔም የገ​ለ​ዓ​ድን ሰዎች ሁሉ ሰበ​ሰበ፤ ከኤ​ፍ​ሬ​ምም ጋር ተዋጋ፤ ኤፍ​ሬ​ምም፥ “ገለ​ዓ​ዳ​ው​ያን ሆይ! እና​ንተ በኤ​ፍ​ሬ​ምና በም​ናሴ መካ​ከል የተ​ቀ​መ​ጣ​ችሁ ከኤ​ፍ​ሬም ሸሽ​ታ​ችሁ ነው” ስላሉ የገ​ለ​ዓድ ሰዎች ኤፍ​ሬ​ምን መቱ።


አባ​ቴስ ለእ​ና​ንተ እንደ ተጋ​ደለ፥ በፊ​ታ​ች​ሁም ሰው​ነ​ቱን ለሞት አሳ​ልፎ እንደ ሰጠ፥ ከም​ድ​ያ​ምም እጅ እንደ አዳ​ና​ችሁ፥


ነፍ​ሱ​ንም በእጁ ጥሎ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ዉን ገደለ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ርሱ ታላቅ መድ​ኀ​ኒት አደ​ረገ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ አይ​ተው ደስ አላ​ቸው፤ በከ​ንቱ ዳዊ​ትን ትገ​ድ​ለው ዘንድ ስለ​ምን በን​ጹሕ ደም ላይ ትበ​ድ​ላ​ለህ?”


ሴቲ​ቱም ወደ ሳኦል መጣች፤ እጅ​ግም ደን​ግጦ እንደ ነበር አይታ፥ “እነሆ፥ እኔ አገ​ል​ጋ​ይህ ቃል​ህን ሰማሁ፤ ነፍ​ሴ​ንም በእጄ ጣልሁ፤ የነ​ገ​ር​ኸ​ኝ​ንም ቃል ሰማሁ።


跟着我们:

广告


广告