Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 11:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሴዎ​ን​ንና ሕዝ​ቡን ሁሉ በእ​ስ​ራ​ኤል እጅ አሳ​ልፎ ሰጠ፤ ገደ​ሉ​አ​ቸ​ውም፤ እስ​ራ​ኤ​ልም በዚያ ምድር ተቀ​ም​ጠው የነ​በ​ሩ​ትን የአ​ሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንን ምድር ሁሉ ወረሱ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 “ከዚያም የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሴዎንንና ሕዝቡን ሁሉ በእስራኤል እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፤ አሸነፏቸውም። እስራኤልም በዚያ አገር የሚኖሩትን የአሞራውያንን ምድር በሙሉ ወረሰ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 “ከዚያም የእስራኤል አምላክ ጌታ ሴዎንንና ሕዝቡን ሁሉ በእስራኤል እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፤” አሸነፏቸውም፤ እስራኤልም በዚያ አገር የሚኖሩትን የአሞራውያንን ምድር በሙሉ ወረሰ፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ነገር ግን የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እስራኤላውያን በሠራዊቱ ላይ ድልን እንዲቀዳጁ አደረገ። በዚህም ዐይነት እስራኤላውያን በዚያ አገር ይኖሩ የነበሩትን የአሞራውያንን ግዛት በሙሉ ወስደው የራሳቸው ርስት አደረጉት፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 የእስራኤልም አምላክ እግዚአብሔር ሴዎንና ሕዝቡን ሁሉ በእስራኤል እጅ አሳልፎ ሰጠ፥ መቱአቸውም፥ እስራኤልም በዚያ ምድር ተቀምጠው የነበሩትን የአሞራውያንን ምድር ሁሉ ወረሰ።

参见章节 复制




መሳፍንት 11:21
8 交叉引用  

የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ከይ​ሁዳ ሰዎች ፊት ሸሹ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ጃ​ቸው አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው።


የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ መን​ግ​ሥ​ትን ለዳ​ዊ​ትና ለል​ጆቹ በጨው ቃል ኪዳን ለዘ​ለ​ዓ​ለም እንደ ሰጠ በውኑ አታ​ው​ቁ​ምን?


ድን​በ​ር​ህ​ንም ከኤ​ር​ትራ ባሕር እስከ ፍል​ስ​ጥ​ኤም ባሕር፥ ከም​ድረ በዳም እስከ ታላቁ እስከ ኤፍ​ራ​ጥስ ወንዝ ድረስ አሰ​ፋ​ለሁ፤ በም​ድር የሚ​ኖ​ሩ​ትን በእ​ጅህ እጥ​ላ​ለ​ሁና፤ ከአ​ን​ተም አስ​ወ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ።


እኔ ግን ቁመቱ እንደ ዝግባ ቁመት፥ ብር​ታ​ቱም እንደ ወይራ ዛፍ የነ​በ​ረ​ውን አሞ​ራ​ዊ​ውን ከፊ​ታ​ቸው አጠ​ፋሁ፤ ፍሬ​ው​ንም ከላዩ፥ ሥሩ​ንም ከታቹ አጠ​ፋሁ።


እስ​ራ​ኤ​ልም በሰ​ይፍ መታው፤ ምድ​ሩ​ንም ከአ​ር​ኖን ጀምሮ እስከ አሞን ልጆች እስከ ያቦቅ ድረስ ወረሰ፤ የአ​ሞ​ንም ልጆች ዳርቻ ኢያ​ዜር ነበረ።


ሴዎ​ንም ሕዝ​ቡም ሁሉ ሊዋ​ጉን ወደ ኢያሳ ወጡ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኢያ​ሱን አለው፥ “እነሆ፥ ኢያ​ሪ​ኮ​ንና ንጉ​ሥ​ዋን ጽኑ​ዓን፥ ኀያ​ላ​ን​ዋ​ንም በእ​ጅህ ሰጥ​ቼ​አ​ለሁ።


ሴዎ​ንም እስ​ራ​ኤል በድ​ን​በሩ እን​ዲ​ያ​ልፍ እንቢ አለ፤ ነገር ግን ሴዎን ሕዝ​ቡን ሁሉ ሰበ​ሰበ፤ በኢ​ያ​ሴ​ርም ሰፈረ፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ጋር ተዋጋ።


跟着我们:

广告


广告