Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 11:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 የገ​ለ​ዓ​ድም ሚስት ወን​ዶች ልጆ​ችን ወለ​ደ​ች​ለት፤ ልጆ​ች​ዋም ባደጉ ጊዜ ዮፍ​ታ​ሔን፥ “የሌላ ሴት ልጅ ነህና በአ​ባ​ታ​ችን ቤት አት​ወ​ር​ስም” ብለው አስ​ወ​ጡት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 እንደዚሁም የገለዓድ ሚስት ለገለዓድ ወንዶች ልጆች ወለደችለት፤ እነርሱም ባደጉ ጊዜ ዮፍታሔን፣ “ከሌላ ሴት ስለ ተወለድህ ከቤተ ሰባችን ምንም ዐይነት ውርስ አይገባህም” በማለት አሳደዱት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 የገለዓድ ሚስትም ለገለዓድ ወንዶች ልጆች ወለደችለት፤ እነርሱም ባደጉ ጊዜ ዮፍታሔን፥ “ከሌላ ሴት ስለተወለድህ ከቤተሰባችን ምንም ዓይነት ውርስ አይገባህም” በማለት አሳደዱት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 የእርሱ አባት ገለዓድ ቀደም ብሎ ያገባት ሚስቱ የወለደችለት ሌሎች ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ እነርሱም ባደጉ ጊዜ ወንድማቸውን ዮፍታሔን “አንተ ከሌላ ሴት የተወለድክ ስለ ሆንክ ከአባታችን ርስት ምንም ነገር መውረስ አይገባህም” ብለው ከቤት እንዲባረር አደረጉት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 የገለዓድም ሚስት ወንዶች ልጆችን ወለደችለት፥ ልጆችዋም ባደጉ ጊዜ ዮፍታሔን፦ የልዩ ሴት ልጅ ነህና በአባታችን ቤት አትወርስም ብለው አሳደዱት።

参见章节 复制




መሳፍንት 11:2
10 交叉引用  

በም​ድ​ርም ራብ ሆነ፤ አብ​ራ​ምም በዚያ በእ​ን​ግ​ድ​ነት ይቀ​መጥ ዘንድ ወደ ግብፅ ወረደ፤ በም​ድር ራብ ጠንቶ ነበ​ረና።


ሣራም አብ​ር​ሃ​ምን አለ​ችው፥ “ይህ​ችን ባሪያ ከነ​ል​ጅዋ አባ​ር​ራት፤ የዚ​ህች ባሪያ ልጅ ከልጄ ከይ​ስ​ሐቅ ጋር አይ​ወ​ር​ስ​ምና።”


ከቀናች መንገድ እንዳያርቁህ፥ እውነትንም ከማወቅ የተለየህ እንዳያደርጉህ፤ ልጄ ሆይ፥ በሕፃንነትህ ትምህርትን የምታስተው፥ ክፉ ምክር አታግኝህ፤


ልጄ ሆይ፥ ከሌላዪቱ ሴት ጋር አትኑር፤ የአንተ ወዳልሆነችውም እጅህን አትዘርጋ።


ከአመንዝራ ሴት ከንፈር ማር ይንጠባጠባልና፥ ወደ አመንዝራ ሴት አትመልከት፥ ለጊዜው ጕሮሮህን ያጣፍጣል፥


ነገር ግን መጽ​ሐፍ ምን ይላል? “የባ​ሪ​ያ​ዪቱ ልጅ ከእ​መ​ቤ​ቲቱ ልጅ ጋር አይ​ወ​ር​ስ​ምና ባሪ​ያ​ዪ​ቱን ከል​ጅዋ ጋር አስ​ወ​ጥ​ተህ ስደ​ዳት”


ዲቃላ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አይ​ግባ፤


ገለ​ዓ​ዳ​ዊ​ዉም ዮፍ​ታሔ ጽኑዕ ኀያል ሰው የጋ​ለ​ሞታ ሴትም ልጅ ነበረ። ለገ​ለ​ዓ​ድም ዮፍ​ታ​ሔን ወለ​ደ​ች​ለት።


ዮፍ​ታ​ሔም ከወ​ን​ድ​ሞቹ ፊት ሸሽቶ በጦብ ምድር ተቀ​መጠ፤ ድሆች ሰዎ​ችም ተሰ​ብ​ስ​በው ዮፍ​ታ​ሔን ተከ​ተ​ሉት።


跟着我们:

广告


广告