Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 10:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 የአ​ሞ​ንም ልጆች ወጥ​ተው በገ​ለ​ዓድ ሰፈሩ። የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ተሰ​ብ​ስ​በው በመ​ሴፋ ሰፈሩ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 አሞናውያን ለጦርነት ዝግጁ ሆነው በገለዓድ በሰፈሩ ጊዜ፣ እስራኤላውያንም እንደዚሁ ተሰብስበው በምጽጳ ሰፈሩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 አሞናውያን ለጦርነት ዝግጁ ሆነው በገለዓድ በሰፈሩ ጊዜ፥ እስራኤላውያንም እንደዚሁ ተሰብስበው በምጽጳ ሰፈሩ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ከዚህ በኋላ የዐሞናውያን ሠራዊት ለጦርነት ተዘጋጅቶ በገለዓድ ሰፈረ፤ የእስራኤልም ሰዎች በአንድነት ተሰብስበው በገለዓድ ምጽጳ ተብሎ በሚጠራው ቦታ ሰፈሩ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 የአሞንም ልጆች ተሰብስበው በገለዓድ ሰፈሩ። የእስራኤልም ልጆች ተሰብስበው በምጽጳ ሰፈሩ።

参见章节 复制




መሳፍንት 10:17
9 交叉引用  

ላባም አለው፥ “እኛ አን​ዳ​ችን ከሌ​ላው እን​ለ​ያ​ያ​ለ​ንና ራእ​ይን የገ​ለ​ጠ​ልኝ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ኔና በአ​ንተ መካ​ከል ሆኖ ይመ​ል​ከት።


ከሐ​ሴ​ቦን ጀምሮ እስከ አራ​ቦት መሴፋ፥ እስከ ቦጣ​ኒም ድረስ፥ ከማ​ኦን ጀምሮ እስከ ዴቦን ዳርቻ ድረስ፥


የገ​ለ​ዓድ ሕዝብ አለ​ቆ​ችም እርስ በር​ሳ​ቸው፥ “ከአ​ሞን ልጆች ጋር መዋ​ጋ​ትን የሚ​ጀ​ምር ማን ነው? እርሱ በገ​ለ​ዓድ ሰዎች ሁሉ ላይ አለቃ ይሆ​ናል” አሉ።


ዮፍ​ታ​ሔም ከገ​ለ​ዓድ ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ጋር ሄደ፤ ሕዝ​ቡም መስ​ፍን ይሆ​ና​ቸው ዘንድ በላ​ያ​ቸው አለቃ አድ​ር​ገው ሾሙት፤ ዮፍ​ታ​ሔም ቃሉን ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በመ​ሴፋ ተና​ገረ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ በዮ​ፍ​ታሔ ላይ መጣ፤ እር​ሱም የም​ናሴ ዕጣ ከም​ት​ሆን ከገ​ለ​ዓድ ምድ​ርና ከገ​ለ​ዓድ መሴፋ፥ ወደ አሞን ልጆች ማዶ ተሻ​ገረ።


ዮፍ​ታ​ሔም ወደ መሴፋ ወደ ቤቱ ተመ​ለሰ፤ እነ​ሆም፥ ልጁ ከበሮ ይዛ እየ​ዘ​ፈ​ነች ልት​ቀ​በ​ለው ወጣች፤ ለእ​ር​ሱም የሚ​ወ​ድ​ዳት አን​ዲት ብቻ ነበ​ረች። ከእ​ር​ስ​ዋም በቀር ወንድ ወይም ሴት ሌላ ልጅ አል​ነ​በ​ረ​ውም።


ከዚ​ያም ወራት በኋላ የአ​ሞን ልጆች እስ​ራ​ኤ​ልን ተዋ​ጉ​አ​ቸው።


ዮፍ​ታ​ሔ​ንም፥ “ና፥ ከአ​ሞን ልጆች ጋር እን​ድ​ን​ዋጋ መስ​ፍን ሁነን” አሉት።


ሳሙ​ኤ​ልም፥ “እስ​ራ​ኤ​ልን ሁሉ ወደ መሴፋ ሰብ​ስቡ፤ ስለ እና​ን​ተም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጸ​ል​ያ​ለሁ” አለ።


跟着我们:

广告


广告