መሳፍንት 10:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)16 ሌሎችንም አማልክት ከመካከላቸው አስወገዱ፤ እግዚአብሔርንም ብቻ አመለኩ፤ ደስም አሰኙት፤ የእስራኤልም ልጆች ከሥቃይ የተነሣ አእምሮአቸውን አጥተው ነበር። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም16 ከዚያም በመካከላቸው ያሉትን ባዕዳን አማልክት አስወገዱ፤ እግዚአብሔርንም አመለኩ፤ እግዚአብሔርም እስራኤል ስትጐሳቈል ዝም ብሎ ማየት አልቻለም። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)16 ከዚያም በመካከላቸው ያሉትን ባዕዳን አማልክት አስወገዱ፤ ጌታንም አመለኩ፤ እርሱም የእስራኤልን መከራ ሊታገሠው የማይቻለው ሆነ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም16 ባዕዳን አማልክታቸውንም አስወግደው፥ እግዚአብሔርን አመለኩ፤ እግዚአብሔርም ስለ እስራኤል መከራ እጅግ አዘነ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)16 ሌሎችንም አማልክት ከመካከላቸው አስወገዱ፥ እግዚአብሔርንም አመለኩ፥ ነፍሱም ስለ እስራኤል ጉስቁልና አዘነች። 参见章节 |