5 ለአዳም ብቻ ከአራዊትና ከእንስሳት ሁሉ ተለይቶ፥ ኀፍረቱን ይሸፍን ዘንድ ልብስን ሰጠው። ስለዚህ የሕግን ፍርድ በሚያውቁ ሰዎች ሁሉ ላይ ኀፍረታቸውን እንዲሰውሩ እንጂ፥ አሕዛብም እንደሚገለጡ እንዳይገለጡ በሰማይ ጽላት ታዘዘ።