36 በዐሥራ አምስተኛው ኢዮቤልዩ በሦስተኛው ሱባዔ ላሜህ ሚስት አገባ፤ ስምዋም ቤቴናስ ይባላል፥ ይህችውም የአባቱ የእኅት ልጅ የበራኪኤም ልጅ ናት፤ ሚስት ትሆነው ዘንድም አገባት።