8 በመጀመሪያዪቱ ሱባዔ አዳም ተፈጠረ፤ ሚስቱም የተገኘችበት ጎኑ ተፈጠረ፤ በሁለተኛዪቱም ሱባዔ እርስዋን አሳየው፤ ስለዚህም በሕርስ ጊዜ ለወንድ ልጅ አንድ ሱባዔ፥ ለሴት ልጅ ሁለት ሱባዔ የመጠበቅ ትእዛዝ ተሰጠ።