3 በእነዚህም በአምስቱ ቀኖች አዳም እነዚህን ሁሉ፥ በምድር ያለውንም ፍጥረት ሁሉ ሴትና ወንድ ሆነው ያይ ነበር። እርሱ ግን ብቻውን ነበረ። እንደ እርሱ ያለ ረዳትንም ለራሱ አላገኘም ነበር።