10 ከዚህም በኋላ ወደ ኤዶም ገነት ገባች፤ ስለዚህ ለምትወልድ ሴት በጽላተ ሰማይ ሥርዐት ተጻፈ። ወንድ ልጅ ብትወልድ እንደ መጀመሪያው ሰባት ቀን በአራስነቷ ሰባት ቀን ትቈያለች፥ ሠላሳ ሦስት ቀንም በመንጻቷ ደም ትቈያለች።