1 በሁለተኛዉ ሱባዔ በስድስቱ ቀናት በእግዚአብሔር ቃል አራዊትን ሁሉ፥ እንስሳትን ሁሉ፥ አዕዋፍን ሁሉና በምድር የሚንቀሳቀሰውን ፍጥረት ሁሉ፥ በውኃውም ውስጥ የሚንቀሳቀሰውን ፍጥረት ሁሉ በየወገናቸውና በየመልካቸው ወደ አዳም አመጣን።