8 እነርሱም በሰባተኛዪቱ ቀን ለመብላትና ለመጠጣት፥ ሁሉን የፈጠረ እግዚአብሔርንም ለማመስገን ከእኛ ጋር ነበሩ። ከእኛ ጋርም በአንድነት ያርፉ ዘንድ ከአሕዛብ ሁሉ ተለይቶ የሚታይ ሕዝብን ባረከ፥ ቀደሰም።