9 በሁለተኛዪቱም ቀን በሐኖስና በውቅያኖስ መካከል ጠፈርን አድርጎአልና፤ በዚያችም ቀን ውኃዎች ተከፍለው እኩሌቶቹ ወደ ላይ ወጥተዋልና፤ እኵሌቶቹ ከጠፈር በታች ወዳለው ወደ ምድር መካከል ወርደዋልና፤ በሁለተኛው ቀን ይህን ሥራ ብቻ ሠራ።