5 በሰባተኛዪቱም ቀን እንዳረፈ፥ ከዕለታቱም ሁሉ እንደ ለያት፥ ለሥራውም ሁሉ ምልክት አድርጎ እንዳኖራት ጻፍ። በመጀመሪያዪቱ ቀን በላይ ያሉ ሰማዮችን ፈጥሮአልና፤ ምድርንና ውኃዎችንም፥ በፊቱ የሚያገለግል ፍጥረትንም ሁሉ ፈጥሮአልና።