16 ፀሓይም ሕይወት ሊሆናቸው በእነርሱ ላይ ወጥቶአልና፥ በዚህ ዓለም በሚኖር ፍጥረትና በምድር በሚበቅለው ሁሉ ላይ፥ በሚያፈራውም እንጨት ሁሉ ላይ፥ በሥጋዊ ደማዊ ሁሉ ላይ ወጥቶአልና፤ በአምስተኛዪቱ ቀን እነዚህን ሦስቱን ፍጥረታት ሁሉ ፈጠረ።