15 በአምስተኛዪቱም ቀን በጥልቅ ውኃዎች መካከል ያሉትን ታላላቅ ዓሣ አንበሪዎች ፈጠረ። ይህ ሁሉ መጀመሪያ በእጁ ተፈጥሮአልና፤ ሥጋዊ ደማዊ ሁሉ፥ በውኃዎችም ውስጥ የሚመላለስ ፍጥረት ሁሉ፥ ዓሣዎችና የሚበሩ ወፎች ሁሉ፥ ወገኖቻቸውም ሁሉ ተፈጥረዋልና፤