13 በአራተኛዪቱም ቀን ጨረቃንና ፀሓይን፥ ከዋክብትንም ፈጥሮ በዓለሙ ሁሉ ያበሩ ዘንድ በጠፈር አኖራቸው። ሌሊትንና ቀንንም አስገዛቸው፤ በብርሃንና በጨለማ መካከልም ለመለየት ድንበር አደረጋቸው።