4 ሙሴም በተራራው ላይ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ተቀመጠ። እግዚአብሔርም ያለፈውንና የሚመጣውን፥ ሕጉ የሚጠበቅበትንና አምልኮቱ የሚነገርበትን፥ የዘመኑን ሁሉ አከፋፈል ነገር አመለከተው።