23 አባት እሆናቸዋለሁ፤ እነርሱም ልጆች ይሆኑኛል፤ ሁሉም የሕያው አምላክ ልጆች ይባላሉ። መልአክ ሁሉ፥ ሰውም ሁሉ ያውቃቸዋል። እነርሱ ልጆች እንደ ሆኑ፥ እኔም በሚገባና በእውነት አባታቸው እንደ ሆንሁ፥ እንደምወድዳቸውም ያውቋቸዋል።