17 ሙሴም በግንባሩ ተደፍቶ ጸለየ፤ እንዲህም አለ፥ “አቤቱ፥ አምላኬ፥ በልቡናቸው ስሕተት ይሄዱ ዘንድ ርስትህ የሆኑ ወገኖችህን አትተው። ይገዙአቸውም ዘንድ፥ አንተንም እንዲበድሉ ያደርጓቸው ዘንድ በጠላቶቻቸው በአሕዛብ እጅ አትጣላቸው።