ኢያሱ 9:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)11 ሽማግሌዎቻችንና የሀገራችን ሰዎች ሁሉ፦ ለመንገድ ስንቅ ያዙ፤ ልትገናኙአቸውም ሂዱ፦ እኛ ባሪያዎቻችሁ ነን፤ አሁንም ከእኛ ጋር ቃል ኪዳን አድርጉ በሉአቸው አሉን። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም11 ሽማግሌዎቻችንና በአገራችን የሚኖሩት ሁሉ፣ ‘ለመንገዳችሁ የሚሆን ስንቅ ያዙ፤ ሄዳችሁም ተገናኟቸው፤ “እኛ ባሮቻችሁ እንሆናለን፤ ከእኛ ጋራ ቃል ኪዳን ግቡ” በሏቸው’ አሉን። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)11 ሽማግሌዎቻችንም በምድራችንም የሚኖሩት ሁሉ እንዲህ አሉን፦ ‘ለመንገድ ስንቅ በእጃችሁ ያዙ፥ ልትገናኙአቸውም ሂዱ እንዲህም በሉአቸው፦ “እኛ ባርያዎቻችሁ ነን፤ እንግዲህ አሁን ከእኛ ጋር ቃል ኪዳን አድርጉ።” ’ 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም11 መሪዎቻችንና በምድራችን የሚኖሩት ሕዝቦች ሁሉ ለመንገዳችን የሚሆነንን ስንቅ አዘጋጅተን መጥተን ከእናንተ ጋር እንድንገናኝ ልከውናል፤ ለእናንተ የምንታዘዝ አገልጋዮች እንድንሆንና እናንተም ከእኛ ጋር የሰላም ውል እንድታደርጉ እንጠይቃችሁ ዘንድ አዘውናል። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)11 ሽማግሌዎቻችንም በምድራችንም የሚኖሩት ሁሉ፦ ለመንገድ ስንቅ በእጃችሁ ያዙ፥ ልትገናኙአቸውም ሂዱ፦ እኛ ባሪያዎቻችሁ ነን፥ አሁንም ከእኛ ጋር ቃል ኪዳን አድርጉ በሉአቸው አሉን። 参见章节 |