Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢያሱ 8:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 ኢያ​ሱም ከተ​ማ​ዋን በእ​ሳት አቃ​ጠ​ላት፤ ዐመ​ድም ሆነች፤ እስከ ዛሬም ድረስ ለዘ​ለ​ዓ​ለሙ የሚ​ኖ​ር​ባት እን​ዳ​ይ​ኖር አደ​ረ​ጋት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 ስለዚህ ኢያሱ ጋይን አቃጠላት፤ እስከ ዛሬ እንደሚታየውም ለዘላለም የዐመድ ቍልልና ባድማ አደረጋት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 ኢያሱም ጋይን አቃጠላት፥ እስከ ዛሬም ድረስ የፍርስራሽ ክምር ለዘለዓለም አደረጋት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 ኢያሱ የዐይን ከተማ በማቃጠል ለዘለዓለም ፍርስራሽ አድርጎ ተዋት፤ እስከ አሁንም ድረስ በዚህ ዐይነት ትገኛለች።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 ኢያሱም ጋይን አቃጠላት፥ እስከ ዛሬም ድረስ ድብድባና በረሃ ለዘላለም አደረጋት።

参见章节 复制




ኢያሱ 8:28
11 交叉引用  

“እኔ ጥን​ቱን እንደ ሠራ​ሁት፥ ቀድ​ሞ​ው​ንም እን​ዳ​ደ​ረ​ግ​ሁት አል​ሰ​ማ​ህ​ምን? አሁ​ንም የተ​መ​ሸ​ጉ​ትን ከተ​ሞች የፍ​ር​ስ​ራሽ ክምር እስ​ኪ​ሆኑ ድረስ እን​ድ​ታ​ፈ​ርስ አደ​ረ​ግ​ሁህ።


ስለ ደማ​ስቆ የተ​ነ​ገረ ቃል። “እነሆ፥ ደማ​ስቆ ከከ​ተ​ሞች መካ​ከል ተለ​ይታ ትጠ​ፋ​ለች፤ ትፈ​ር​ሳ​ለ​ችም።


ከተ​ሞ​ችን ትቢያ አደ​ረ​ግህ፤ የተ​መ​ሸጉ ከተ​ሞ​ችን፥ የኃ​ጥ​ኣ​ን​ንም መሠ​ረት አፈ​ረ​ስህ፤ ከተ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም ለዘ​ለ​ዓ​ለም አይ​ሠ​ሩም።


ስለ​ዚህ እነሆ በአ​ሞን ልጆች ከተማ በራ​ባት ላይ የሰ​ልፍ ውካ​ታን የማ​ሰ​ማ​በት ዘመን ይመ​ጣል፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ለጥ​ፋ​ትም ትሆ​ና​ለች፥ መን​ደ​ሮ​ች​ዋም በእ​ሳት ይቃ​ጠ​ላሉ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም የወ​ረ​ሱ​ትን ይወ​ር​ሳል፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ጊዜዋ ደር​ሶ​አ​ልና ሣጥ​ኖ​ች​ዋን ከፍ​ታ​ችሁ እንደ ዋሻ በር​ብ​ሯት፤ ጨር​ሳ​ች​ሁም አጥ​ፏት፥ ምንም አታ​ስ​ቀ​ሩ​ላት።


ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም የፍ​ር​ስ​ራሽ ክምር፥ የቀ​በ​ሮም ማደ​ሪያ አደ​ር​ጋ​ታ​ለሁ፤ የይ​ሁ​ዳ​ንም ከተ​ሞች ሰው እን​ዳ​ይ​ቀ​መ​ጥ​ባ​ቸው አጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለሁ።


ስለዚህ በእናንተ ምክንያት ጽዮን እንደ እርሻ ትታረሳለች፥ ኢየሩሳሌም የድንጋይ ክምር ትሆናለች፥ የቤቱም ተራራ እንደ ዱር ከፍታ ይሆናል።


ዕቃ​ዋ​ንም ሁሉ ወደ አደ​ባ​ባ​ይዋ ትሰ​በ​ስ​ባ​ለህ፤ ከተ​ማ​ይ​ቱ​ንም፥ ዕቃ​ዋ​ንም ሁሉ በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በእ​ሳት ፈጽ​መህ ታቃ​ጥ​ላ​ለህ፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ወና ትሆ​ና​ለች፤ ደግ​ሞም አት​ሠ​ራም።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የመ​ቅ​ሠ​ፍቱ ቍጣ ይመ​ለስ ዘንድ፥ ለአ​ባ​ቶ​ች​ህም እንደ ማለ​ላ​ቸው ይም​ርህ ዘንድ፥ ይራ​ራ​ል​ህም ዘንድ፥ ያበ​ዛ​ህም ዘንድ፥ ርጉም ከሆ​ነው አን​ዳች ነገር በእ​ጅህ አት​ንካ።


ኢያ​ሱም የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት የተ​ሸ​ከሙ ካህ​ናት እግ​ሮች በቆ​ሙ​በት ስፍራ በዮ​ር​ዳ​ኖስ መካ​ከል ሌሎች ዐሥራ ሁለት ድን​ጋ​ዮ​ችን አቆመ፤ እስከ ዛሬም ድረስ በዚያ አሉ።


የጋ​ይ​ንም ንጉሥ በዝ​ግባ ዛፍ ላይ ሰቀ​ለው፤ እስከ ማታም ድረስ በዛፉ ላይ ቈየ። ፀሐ​ይም በገ​ባች ጊዜ ኢያሱ ያወ​ር​ዱት ዘንድ አዘዘ፤ ከዛ​ፉም አወ​ረ​ዱት፤ በከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም በር አደ​ባ​ባይ ጣሉት፤ በላ​ዩም እስከ ዛሬ ድረስ ያለ​ውን ታላቅ የድ​ን​ጋይ ክምር ከመ​ሩ​በት።


跟着我们:

广告


广告