ኢያሱ 8:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)18 እግዚአብሔርም ኢያሱን፥ “ጋይን በእጅህ አሳልፌ እሰጥሃለሁና በእጅህ ያለውን ጦር በላይዋ ዘርጋ፤ ከተማዪቱንም የከበቡአት ፈጥነው ከስፍራቸው ይነሣሉ” አለው፤ ኢያሱም በከተማዋ ላይ በእጁ ያለውን ጦር ዘረጋ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም18 እግዚአብሔርም ኢያሱን፣ “ከተማዪቱን በእጅህ አሳልፌ እሰጥሃለሁ፣ የያዝኸውን ጦር ወደ ጋይ አነጣጥር” አለው፤ ኢያሱም ጦሩን ወደ ጋይ አነጣጠረ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)18 ጌታ ኢያሱን እንዲህ አለው፦ “ጋይን በእጅህ አሳልፌ እሰጥሃለሁና በእጅህ ያለውን ጦር በእርሷ ላይ ዘርጋ፤” ኢያሱም በእጁ ያለውን ጦር በከተማይቱ ላይ ዘረጋ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም18 ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር ኢያሱን፦ “ጦርህን በዐይ ከተማ ላይ አንሣ፤ እኔ እርስዋን ለአንተ አሳልፌ እሰጥሃለሁ” አለው። ኢያሱም በእጁ ያለውን ጦር ወደ ከተማይቱ ዘረጋ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)18 እግዚአብሔር ኢያሱን፦ ጋይን በእጅህ አሳልፌ እሰጥሃለሁና በእጅህ ያለውን ጦር በላይዋ ዘርጋ አለው፥ ኢያሱም በእጁ ያለውን ጦር በከተማይቱ ላይ ዘረጋ። 参见章节 |