ኢያሱ 7:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)7 ኢያሱም አለ፥ “ወዮ! ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! በአሞሬዎናውያን እጅ አሳልፈህ ትሰጠን፥ ታጠፋንም ዘንድ አገልጋይህ ይህን ሕዝብ ዮርዳኖስን ለምን አሻገረ? በዮርዳኖስ ማዶ ተቀምጠን በኖርን ነበር እኮ! 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም7 ኢያሱም እንዲህ አለ፤ “ወዮ! ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ ዮርዳኖስን አሻግረህ ይህን ሕዝብ ወደዚህ ያመጣኸው ለአሞራውያን አሳልፈህ በመስጠት እንዲያጠፉን ነውን? ምነው ሳንሻገር እዚያው ማዶ በቀረን ኖሮ! 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)7 ኢያሱም እንዲህ አለ፦ “ወዮ! ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! በአሞራውያን እጅ አሳልፈህ ልትሰጠን ልታጠፋንም ይህን ሕዝብ ዮርዳኖስን ለምን አሻገርኸው? በዮርዳኖስ ማዶ መቀመጥን በወደድን ነበር እኮ! 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም7 ኢያሱም እንዲህ ሲል ጸለየ፦ “ወዮ! እግዚአብሔር አምላክ ሆይ! ይህን ሕዝብ ለምን ዮርዳኖስን አሻገርከው? አሞራውያን እንዲያጠፉን ለእነርሱ አሳልፈህ ለመስጠት ነውን? ከዮርዳኖስ ማዶ ብንቀመጥ እንዴት በተሻለን ነበር! 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)7 ኢያሱም አለ፦ ዋይ! ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ በአሞራውያን እጅ አሳልፈህ ትሰጠን ታጠፋንም ዘንድ ይህን ሕዝብ ዮርዳኖስን ለምን አሻገርኸው? በዮርዳኖስ ማዶ መቀመጥን በወደድን ነበር እኮ! 参见章节 |