Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢያሱ 4:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ኢያ​ሱም የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት የተ​ሸ​ከሙ ካህ​ናት እግ​ሮች በቆ​ሙ​በት ስፍራ በዮ​ር​ዳ​ኖስ መካ​ከል ሌሎች ዐሥራ ሁለት ድን​ጋ​ዮ​ችን አቆመ፤ እስከ ዛሬም ድረስ በዚያ አሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ኢያሱም የቃል ኪዳኑን ታቦት የተሸከሙት ካህናት ቆመውበት በነበረው በዮርዳኖስ ወንዝ መካከል ሌሎች ዐሥራ ሁለት ድንጋዮችን አቆመ፤ እነዚህም ድንጋዮች እስከ ዛሬ ድረስ በዚሁ ስፍራ ይገኛሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ኢያሱም የቃል ኪዳኑን ታቦት የተሸከሙ ካህናት እግሮች በቆሙበት ስፍራ በዮርዳኖስ መካከል ሌሎችን ዐሥራ ሁለት ድንጋዮች አኖረ፤ እስከ ዛሬም ድረስ በዚያ አሉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ኢያሱም ደግሞ ካህናቱ የቃል ኪዳኑን ታቦት ተሸክመው በቆሙበት በዮርዳኖስ ወንዝ መካከል ዐሥራ ሁለት የመታሰቢያ ድንጋዮችን አቆሙ፤ እነዚያም ድንጋዮች እስከ ዛሬ በዚያው ይገኛሉ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ኢያሱም የቃል ኪዳኑን ታቦት የተሸከሙ ካህናት እግሮች በቆሙበት ስፍራ በዮርዳኖስ መካከል ሌሎችን አሥራ ሁለት ድንጋዮች ተከለ፥ እስከ ዛሬም ድረስ በዚያ አሉ።

参见章节 复制




ኢያሱ 4:9
16 交叉引用  

ስም​ዋ​ንም “መሐላ” ብሎ ጠራት፤ ስለ​ዚ​ህም የከ​ተ​ማ​ዪቱ ስም እስከ ዛሬ ድረስ “ዐዘ​ቅተ መሐላ” ይባ​ላል።


ያዕ​ቆ​ብም ማልዶ ተነሣ፤ ተን​ተ​ር​ሷት የነ​በ​ረ​ች​ው​ንም ድን​ጋይ ወስዶ ሐው​ልት አድ​ርጎ አቆ​ማት፥ በላ​ይ​ዋም ዘይ​ትን አፈ​ሰ​ሰ​ባት።


ቤሮ​ታ​ው​ያ​ንም ወደ ጌቴም ሸሽ​ተው ነበር፤ እስከ ዛሬም ድረስ በዚያ ተጠ​ግ​ተው ነበር።


ኤል​ያ​ስም፦ ስምህ እስ​ራ​ኤል ይሆ​ናል የሚል የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል እንደ ደረ​ሰ​ለት እንደ እስ​ራ​ኤል ልጆች ነገድ ቍጥር ዐሥራ ሁለት ድን​ጋ​ዮ​ችን ወሰደ።


መሎ​ጊ​ያ​ዎ​ቹም ረጃ​ጅ​ሞች ነበ​ሩና በቅ​ድ​ስተ ቅዱ​ሳኑ ፊት ከመ​ቅ​ደሱ ውስጥ ጫፎ​ቻ​ቸው ይታዩ ነበር፤ ነገር ግን ከውጭ አይ​ታ​ዩም ነበር፤ እስከ ዛሬም ድረስ እዚያ አሉ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “ወደ እኔ ወደ ተራ​ራው ውጣ፤ በዚ​ያም ሁን፤ እኔ የጻ​ፍ​ሁ​ትን ሕግና ትእ​ዛዝ፥ የድ​ን​ጋ​ይም ጽላት እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ፤ ሕግ​ንም ትሠ​ራ​ላ​ቸ​ዋ​ለህ” አለው።


የዕ​ን​ቍም ድን​ጋ​ዮች እንደ እስ​ራ​ኤል ልጆች ስሞች ዐሥራ ሁለት ይሆ​ናሉ፤ በየ​ስ​ማ​ቸ​ውም ማኅ​ተም አቀ​ራ​ረጽ ይቀ​ረጹ፤ ስለ ዐሥራ ሁለቱ ነገ​ዶ​ችም ይሁኑ።


ስለዚህ ያ መሬት እስከ ዛሬ ድረስ “የደም መሬት” ተባለ።


እነርሱም ገንዘቡን ተቀብለው እንደ አስተማሩአቸው አደረጉ። ይህም ነገር በአይሁድ ዘንድ እስከ ዛሬ ድረስ ሲወራ ይኖራል።


በቤተ ፌጎ​ርም አቅ​ራ​ቢያ በና​ባው ምድር ቀበ​ሩት፤ እስከ ዛሬም ድረስ መቃ​ብ​ሩን ማንም የሚ​ያ​ውቅ የለም።


ኢያ​ሱም ይህን ቃል ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕግ መጽ​ሐፍ ጻፈው፤ ኢያ​ሱም ታላ​ቁን ድን​ጋይ ወስዶ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በነ​በ​ረ​ችው በአ​ሆማ ዛፍ በታች አቆ​ማት።


ኢያ​ሱም ለሕ​ዝቡ እን​ዲ​ነ​ግር፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዘ​ዘ​ውን ሁሉ እስ​ኪ​ፈ​ጽም ድረስ የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት የተ​ሸ​ከሙ ካህ​ናት በዮ​ር​ዳ​ኖስ መካ​ከል ቆመው ነበር፤ ሕዝ​ቡም ፈጥ​ነው ተሻ​ገሩ።


ሰው​የ​ውም ወደ ኬጤ​ዎ​ና​ው​ያን ምድር ሄደ፤ በዚ​ያም ከተ​ማን ሠራ፤ ስም​ዋ​ንም ሎዛ ብሎ ጠራት። እስከ ዛሬም ድረስ ስምዋ ያው ነው።


ከዚ​ያም ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ይህ ለእ​ስ​ራ​ኤል ሥር​ዐ​ትና ሕግ ሆነ።


ሳሙ​ኤ​ልም አንድ ድን​ጋይ ወስዶ በመ​ሴ​ፋና በአ​ሮ​ጌው ከተማ መካ​ከል አኖ​ረው፤ ስሙ​ንም፥ “እስከ አሁን ድረስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ረድ​ቶ​ናል” ሲል “አቤ​ን​ኤ​ዜር” ብሎ ጠራው። እብነ ረድ​ኤት ማለት ነው።


跟着我们:

广告


广告